የፅህፈት፣ የት/ት፣ የጽዳት እቃዎች፣ ደንብ ልብስ፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ ህትመትና የጥገና ስራዎች ግዥ (11 ሎቶች, 001/2019) - ፊት አውራሪ ኃ/ጊ/ቁ2 አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
ፊት አውራሪ ኃ/ጊ/ቁ2/አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡- 001/2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የፊት አውራሪ ኃ/ጊ/ቁ2/ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን እና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
| ሎት | የዕቃው አይነት | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የብር መጠን 2% |
| 1 | አላቂ የፅህፈት መገልገያ እቃዎች | 2,000.00 |
| 2 | አላቂ የት/ት መሳሪያዎች | 2,000.00 |
| 3 | የጽዳት ዕቃዎች | 2,000.00 |
| 4 | የደንብ ልብስ | 2,500.00 |
| 5 | የተለያዩ ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች | 10,000.00 |
| 6 | የተለያዩ ለጥገና አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች | 2,000.00 |
| 7 | የተለያዩ የህትመት ሥራዎች | 1000.00 |
| 8 | ለፎቶ ኮፒ እና ፕሪንተር ማሽነሪ ጥገና እና ሰርቪስ | 2000.00 |
| 9 | የመስተንግዶ ውሃ/ቆሎ ግዥ | 1000.00 |
| 10 | የመጀመሪያ እርዳታ የህክምና መስጫ እቃዎች እና የላብራቶሪ እቃዎች | 2,500.00 |
| 11 | የተለያዩ የጥገና ስራዎች | 3,000.00 |
በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር www.ppa.gov ውስጥ የተመዘገቡ
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል አንድ ኦርጅናል ኮፒ እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር አንድ ኦርጅናል ኮፒ የድርጅቱ ስም አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ አይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ...ኛው ቀን ድረስ ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ የመጫረቻ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡ ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በት/ቤቱ ላይብረሪ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የመጫረቻ ሰነድ (SBD) በነጋዴ መሞላት ያለበት ቦታ በጥንቃቄ ታይቶ በትክክል መሞላት ይኖርበታል ፤ የመጫረቻ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ መኖር አለበት የጨረታ ሰነድ ሳይገነጣጠል ተመላሽ መሆን አለበት ያልተሟላ የጨረታ ሰነድ ከሆነ ከውድድር ውጪ እንደሚሆን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከሠኞ - አርብ አጠቃላይ የሎት መግዣ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ በአሸነፉበት ሎት ከጠቅላላ ዋጋው 10% ዋጋው በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም የጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታው ካገለለ እና የጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀ በኋላ በተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል በመዋዋል የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ CPO ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሎት1 ፣ ሎት2 ፣ ሎት3 ፣ ሎት4 ፣ ሎት7 እና ሎት9 ላይ ተጫራቹ ናሙና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለበት በተጨማሪም ሎት5 (የተለያዩ ቋሚ የቢሮ መገልገያ እቃዎች) ተጫራች የሚወዳደርበትን እቃ በከለር የተደገፈ ፎቶ እንደ ሳንፕል ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራች በጨረታ ከቀረበው አጭር መግለጫ (specification) ውጪ በመሰረዝ ወይም በማሻሻል ማቅረብ እና በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ መጫረት አይፈቀድም፡፡
- በአነስተኛ እና ጥቃቅን የተደራጁ የራሳቸው እሴት የሌላቸው እና አምራች ያልሆኑ እንደማንኛውም ተወዳዳሪ የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ቼክ (C.P.O) 0.5% ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በማቅረብ መወዳደር ይችላሉ ... በጥቅል ማሰራት አይፈቀድም፡፡
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን እቃ በራሱ የትራንስፖርት ወጪ በመንግሥት የሥራ ሰዓት ... ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የማቅረብ እና የማስረከብ ግዴታ አለበት ከሥራ ሰዓት ውጪ የሚያመጣ ... ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ለጨረታ ከቀረቡ እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሀያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- ስ.ቁጥር 011-2-73-10-14
አድራሻ፡- አስኮ ሊዝ መንደር ከሚረር አካዳሚ ት/ቤት ጎን አቢሲኒያ ባንክ ፊት ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ት/ት መምሪያ የፊት አውራሪ ኃ/ጊ/ቁ2 1ኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
Fet Awrari H/G/Qu2 Primary School invites bids for 11 lots covering stationery, educational materials, cleaning supplies, uniforms, office supplies, printing, maintenance services, water, first aid and laboratory items. Bidders need a renewed license, tax compliance, MoFEC and PPA registration, VAT registration, and samples for lots 1,2,3,4,7,9.
