ለሁለተኛ ጊዜ፡ የቢሮ፣ የደንብ ልብስ፣ የስልጠና እና የምርት ስራ ቋሚና አላቂ እቃዎች ግዥ - የሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጎባ
በባሌ ሮቤ በጎባ ክ/ከተማ የ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ለሁለተኛ (2) ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በባሌ ሮቤ በጎባ ክ/ከተማ የሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የቢሮ፣ የደንብ ልብስ፣ ለስልጠና እና ለተለያዩ ለምርት ስራ አገልግሎቶች የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች፤
- ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆኑንና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና ፎቶ ኮፒውን ከጨረታው ሠነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
- ከላይ ለተጠቀሰው እቃ የማወዳደሪያ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50000 (ሀምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ በሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊው የሚያቀርበው እቃ መስፈርቱን የማያሟላ ሆኖ ከተገኘ ለመመለስ ግዴታ የሚገባ መሆን አለበት፡፡
- የሚቀርቡት ሰነዶች ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛ የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት የጨረታው ሠነድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ገብቶ ከታሸገ በኋላ በዚው ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመግዛት ከጎባ ከተማ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የአሸናፊ አቅራቢዎች የውል ማስከበሪያ የእቃውን ሙሉ ዋጋ 10% ኮንትራት አማውንት (በባንክ የተረጋገጠ በሲፒኦ ብቻ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች እቃውን የማጓጓዣ መጫኛና ማውረጃ ወጪውን በመቻል ጎባ ከተማ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
- የእቃዎቹን ዋጋ መስሪያ ቤቱ የሚከፍለው በጥያቄው መሰረት መቅረቡ እና ንብረት ክፍል ገቢ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡
- ተጫራቾች በቀረበው እስፔስፊኬሽን መሰረት ጨረታውን ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው በ 5 (አምስት) ቀን ውስጥ መስሪያ ቤቱ ቀርበው ውል መፈረም ይኖርባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- እቃ ለማቅረብ የምትወዳደሩ በሙሉ በእቃ አቅራቢነት የተመዘገባችሁበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒውን ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- ለበለጠ መረጃ ጎባ ከተማ ሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በስልክ ቁጥር፡- 0920379891 ወይም 0913181413 መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በባሌ ሮቤ በጎባ ክ/ከተማ የሃጅ አደም ሳዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
✨ messages.ai_summary
Haj Adam Sado Polytechnic College in Goba seeks suppliers for office supplies, uniforms, training materials, and production-related fixed and consumable goods. Bidders must be registered taxpayers with valid business licenses and submit CPO-backed bid security. Awarded suppliers must deliver to the college and sign a contract within 5 days of notification.
