የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ – የአዲስ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል ሎት፣ የደንብ ልብስ፣ ሎት 2 የጽሕፈት መሣሪያዎች፣ ሎት 3 ኅትመት ሎት 4 የፅዳት እቃ፣ ሎት 5 ልዩ ልዩ እቃ፣ ሎት 6 የውሃ ግዥ፣ሎት 7 የመኪና እቃ፣ ሎት 8 የቢሮ ዕቃ ጥገና፣ ሎት 9 የአይቲ ዕቃ፣ ሎት 10 ቋሚ እቃ፣ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል:: ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ::
- በጨረታ ለመሳተፍ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ሠርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 መቶ ብር በመክፈል ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናትና ቅዳሜን ሙሉ ቀን ጨምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዊንጌት አደባባይ ድንገተኛ እሳት አደጋ መከላከያ ጎን በሚገኘው ሕንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት በመቅረብ የጨረታ ሠነዱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት ይችላሉ::
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የአንድ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ ዕሴት ታክስን ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታችሁ ማህተምና ፊርማና ሙሉ አድራሻችሁን በግልጽ በመጻፍ የሚወዳደሩበትን ሠነድ ኦርጂናልና ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም የቴክኒክ ዶክመንት ለብቻ በማድረግ በታሸገ ፖስታ መ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት የሚጠበቅባቸው ሲሆን መ/ቤቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማወዳደሪያ ሰንጠረዥ ብቻ መሙላት አለበት::
- ተጫራቾች በተሳተፉበት አቅርቦት ላይ ለመ/ቤቱ የቴክኒክ ኮሚቴዎች ናሙና ለማቅረብ እና ናሙና ለማሳየት ፍቃደኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል እና የጥራት መለኪያ፣ ስፔስፊኬሽን በተጠቃሚ ምርጫ መሆን አለበት::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00/ አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/C.P.O./ በጽ/ቤታችን ስም ማለትም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሚል ስም በማስያዝ ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን ቅዳሜን ጨምሮ ባሉት ቀናት እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታ ሣጥኑ ጨረታው በወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4.30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤታችን በግዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል::
- አሸናፊው ድርጅት የአሸናፊነት ውጤት በደብዳቤ ከተገለጸበት ከሰባተኛው ቀን በኋላ በመቅረብ የውል ማስከበሪያ የመጫረቻ ዋጋውን 10% /አስር ፐርሰንት/CPO በማስያዝ የውል ስምምነት መፈረም ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች በራሳቸው የትራንስፖርት ወጪ ጭነው መ/ቤቱ የእቃ መጋዘን ውስጥ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን እንዲሁም አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም::
- በጨረታው የአሸነፉ ድርጅቶች እቃውን ባያቀርቡ ወይም ውል አንዋዋልም ቢሉ ያሲያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል::
- የጨረታውን ዋጋ 20 % መጨመር ወይም መቀነስ እንደተጠበቀ ይሆናል:: ጨረታው ለ90 ቀናት ጸንቶ ይቆያል::
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ :0112735558 /0112707761/0112706596 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ::
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
Open tender for various goods and services for the 2019 budget year, split into 10 lots: lottery, uniforms, stationery, printing, cleaning materials, miscellaneous items, water, vehicle parts, office equipment repair, IT equipment, and fixed assets. Bidders need a renewed business license, VAT registration, and taxpayer ID. Samples may be required.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
