Tender Detail

Tender Details

  • Company የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address አምቦ ከተማ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0112609448
  • Website
  • Deadline03 Nov 2026, 2:15 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price2000(ሁለት ሺህ ብር)
  • Bid Securityብር 500,000 CPO
  • opening dateበዚሁ ዕለት በ8:45ሰዓት ይከፈታል።
  • Categories Electrical And Electromechanical , Road And Bridge Construction , Building Construction

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የሚዉሉ “Mini-Bridge”፤ G+2 የገበያ ማዕከል ህንፃ፤ “Traditional Court hall” ህንፃ ግንባታ እና የመንገድ ላይ መብራትን ለማስገንባት አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ኮንትራክተሮችን በማወዳደር ለማሰራት ለሚፈልግ፤

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2019

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት የሚዉሉ “Mini-Bridge”፤ G+2 የገበያ ማዕከል ህንፃ፤ “Traditional Court hall” ህንፃ ግንባታ እና የመንገድ ላይ መብራትን ለማስገንባት አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ኮንትራክተሮችን በማወዳደር ለማሰራት ለሚፈልግ፤

ተ/ቁየስራ ዓይነትደረጃኮንትራክተር
1G+2 የገበያ ማዕከል ህንፃ4 እና ከዚያ በላይGC,BC
2“Mini-Bridge”4 እና ከዚያ በላይGC,RC
3Traditional Court hall/ Mana murtii Aadaa OL-daharfataa”4 እና ከዚያ በላይGC,BC
4የመንገድ ላይ መብራት/Street Light/4 እና ከዚያ በላይElectro Mechanical
  1. ከተጠቀሰው ስራ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለው የ 2019 ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin Number/ ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ/VAT/ ተመዝጋቢ፤ እንዲሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር/Supplier List/ የተመዘገበ ሆኖ ከሚመለከተው አካል የማስረጃውን ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል ፤ በተጨማሪም ከሚያገኘው ገቢ ላይ 3% ታክስ ለመክፈል ፈቃደኛ የሆነ፤
  2. ከሙስና እና መሰል ብልሹ አሰራር ድርጊቶች ነፃ የሆነ የክልሉንና የአገሪቱን ሕግ የሚያከብር፤
  3. በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት ስም ብር 500,000 CPO የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችል፤
  4. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስልጣን ባለዉ አካል /የድርጅቱ ባለቤት/ ስም፤ ፊርማ፤ የድርጅቱ ማህተም ፤ የድርጅቱ ሙሉ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር በፖስታ ላይ መግለፅ የሚችል፤
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካል፤ ፋይናንሻል እና CPO ኦሪጂናል እና የቴክኒካል፤ ፋይናንሻል እና CPO ኮፒዎቻቸው በታሸገ ፖስታ አድርጎ ማቅረብ አለበት።
  6. ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 20 ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ21 ቀን በ24/02/2019ዓ/ም በ8:15 የጨረታው ሳጥን ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8:45ሰዓት ይከፈታል።
  7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በአምቦ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ክፍል ይከፈታል። ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ ባለመገኘታቸው ምክንያት ጨረታውን ከመክፈት አየስቀርም፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት የአድራሻ ለውጥ ካለ በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን።
  8. እያንዳንዱን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 2000/ሁለት ሺህ ብር/ በመክፈል በአምቦ ከተማ ገንዘብ ፅ/ቤት ስም በTele birr short Code 518219 እና Operator Id 182149 በማስገባት ደረሰኙን በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ፅ/ቤት ገቢ በማድረግ ሰነዱን በአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት መዉሰድ ይቻላል።
  9. አሸናፊ የሆነ ተጫራች አሸናፊ የሆነበትን ስራ በደብዳቤ ከተሰጠው ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከ/ቤቱ ጋር ውል መፈረም አለበት፡፡
  10. ጨረታዉን ለማደናቀፍ የሚሞክር ተጫራች ከጨረታዉ ዉጪ እንዲሆን ተደርጎ ለወደፊቱ በማንኛውም የመንግስት ግዥ እንዳይሳተፍ ይደረጋል።
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ከገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- በኦሮሚያ ክልል ምዕ/ሸዋ ዞን የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Ambo City Administration Finance Office seeks contractors for construction of a Mini-Bridge, a G+2 market center building, a Traditional Court hall, and street lights. Bidders need a renewed business license, TIN, VAT registration, supplier list registration, and must accept 3% tax.
Save Tender

Supply & Fix Alarm System and Supply of Light Fitting and Distribution Board - Federal Auditor Gener...

READ MORE