Supply & Fix Alarm System and Supply of Light Fitting and Distribution Board - Federal Auditor General Project (DCE/SF/141/2026 & 142/2026) - የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥሮች DCE/SF/141/2026 እና DCE/SF/142/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት (አዲስ አበባ) ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሠንጠረዥ በዝርዝር የተጠቀሱትን የተለያዩ የአቅርቦት እና ገጠማ ሥራዎች ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የዕቃው አይነት | የፕሮጀክት ስም | የጨረታ ቁጥር | የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ ማስከበሪያ |
| 1 | Supply & fix Alarm system | ፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት (አ/አ) | DCE/SF/141/2026 | ኅዳር 02/2019 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት | ኅዳር 02/2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት | 50,000.00 |
| 2 | Supply of Light Fitting and Distribution board | ፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት (አ/አ) | DCE/SF/142/2026 | ኅዳር 02/2019 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት | ኅዳር 02/2019 ዓ.ም 4፡45 ሰዓት | 50,000.00 |
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ...ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ (Bid Bond) 120 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (CPO) መቅረብ ይኖርባቸዋል። የመንግስት ድርጅቶች ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ለያንዳንዱ ጨረታ ቁጥር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መከፈ ግቢ ውስጥ
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መከፈ ግቢ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0911171751/0913297297
E-mail አድራሻ Info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
✨ messages.ai_summary
Defense Construction Enterprise seeks bidders for the Federal Auditor General project in Addis Ababa: supply and fix an alarm system, and supply light fittings and a distribution board. Bidders must submit a renewed business license, tax clearance, VAT registration, and supplier registration.
