የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በስሩ ለሚገኙ ተቋማት አገልግሎት የሚውል፡- ሎት 1 አመታዊ የመኪና መድን ዋስትና /ኢንሹራንስ ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ሎት 3 ለባህል ቱሪዝም መምሪያ አገልግሎት የሚውል የቦክስ ሪንግ ማቴሪያል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ በስሩ ለሚገኙ ተቋማት አገልግሎት የሚውል፡-
ሎት 1 አመታዊ የመኪና መድን ዋስትና /ኢንሹራንስ
ሎት 2 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
ሎት 3 ለባህል ቱሪዝም መምሪያ አገልግሎት የሚውል የቦክስ ሪንግ ማቴሪያል ግዥ
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለፅን፡-
ማቅረብ የምትችሉት መረጃ፡-
- የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላችሁ
- የግብርመለያ ቁጥር/TIN/ያላቸው
- የዘመኑን ታክስ ለመክፈላቸው ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል
- የገንዘብ መጠኑ ከ500,000 ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይኖርበታል
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚገዛዉን ግዥ ዝርዝርመግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ/ቢድ ቦንድ/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ/ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200/መቶ /በመክፈል ጎን/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሃሳባቸውን አንድ ወጥ በሆነ ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ጎን/ከ/አስ/ግዥና/ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቶች ዋጋውን በሚሞሉበት ወቅት ስርዝ ድልዝ ካለ ከውድድር ውጭ ያስደርጋል
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ሙሉ ስምና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት በጎንደር ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 11 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ 4:00 ታሽጎ 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጥሪአችንን አክብረዉ ባይገኙም ጨረታዉ በሌሉበት ይከፈታል፡፡ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተጠቀሰዉ ሰአት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ ጨረታው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 5 የስራ ቀን ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ የሚቀርብ ቅሬታ መ/ቤታችን የማንቀበል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- የቦክስ ሪንግ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ጎ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ለአመታዊ ኢንሹራንስ ጎ/ከ/አስተዳደር ህጋዊ ቢሮ/ተቋም ያለው መሆን አለበት
- ጨረታ ሲከፈት የተነበበው ዋጋ እና የሂሳብ ስሌት ሲሰራ በሚገኘው ዋጋ ላይ እስከ 3% ልዩነት ከተገኘ ተቀባይነት ሲኖረው ወደ ታችም ሆነ ወደ ላይ ከ3% በላይ ልዩነት ካለ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡ዋጋን ደምሮ አለማስቀመጥም ከውድድር ውጭ ያስደርጋል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ ካስፈለገ ጎን/ከተ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 058 126 03 06 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
P.O.Box 192 Tele: 0581-26-03-06
Fax: 0581 11 7563 email: gontipco@ethionet.et
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
Gondar City Administration Finance Department seeks bidders for three lots: annual vehicle insurance, electronic materials, and boxing ring materials for the Culture and Tourism Department. Bidders must have a valid trade license, TIN, and tax clearance; VAT registration is required if the amount exceeds 500,000 birr.
