Tender Detail

Tender Details

  • Company የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል
  • Address ጅማ ዞን በዴዶ : ኦሮሚያ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 0917878961
  • Website
  • Deadline02 Nov 2026, 4:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/CPO/
  • opening dateበ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Medical Equipment And Supplies , Laboratory Equipment And Chemicals , Furniture

የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና መለዋወጫ፣ የላብራቶሪ ሬጀንት፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ደንብ ልብስ OR፣የቢሮ ዕቃ/ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 ዓ.ም በጀት አመት አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችና መለዋወጫ፣ የላብራቶሪ ሬጀንት፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የጽህፈት መሳሪያ፣ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ደንብ ልብስ OR፣የቢሮ ዕቃ/ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት የጨረታ መስፈርቱን የሚያሟሉ፤

  1. በአከፋፋይነት/በችርቻሮ የዘመኑን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
  2. TIN Number ያለውና VAT ተመዝጋቢ የሆነ፤
  3. ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/CPO/ ማቅረብ የሚችል፤
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፤
  5. ንብረቶችን እስከቦታው ድረስ ማቅረብ የሚችል፤
  6. የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ካቀረበው ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ሁሉንም ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ግ/ክ/ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 40 መግዛት ይቻላል፤
  8. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  9. ጨረታው ይሄ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ ለ15 ስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ተዘግቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ግ/ክ/የስራ ሂደት በዩፋ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ በዓል /ዝግ/ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፤
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል

✨ messages.ai_summary
Tepi General Hospital seeks suppliers for medical equipment and accessories, laboratory reagents, cleaning materials, stationery, electronics, uniforms, and office supplies/furniture via open tender. Eligible bidders must hold a valid trade license, TIN, VAT registration, supplier certificate, and deliver items to site.
Save Tender