Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
  • Address በእስታድየም አካባቢ ይሓ ሲቲ ሴንተር ሕንጻ 6ኛ ፎቅ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115580505
  • Website
  • Deadline23 Oct 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400(አራት መቶ ብር)
  • Bid Securityበሎት: ከብር 3,000.00 እስከ 26,000.00 (CPO)
  • opening dateበ11ኛ ቀን ጥዋት 3:00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ጥዋት 3:30 ሰዓት
  • Categories Printing And Publishing , Office Machines And Computers , Stationery Materials

የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች፣ የጥገናና የእድሳት አገልግሎቶች ግዥ ጨረታ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት


የመጀመሪያ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 01/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ሎቶች የደንብ ልብስና የስራ ልብሶች፣የጽህፈት መሳሪያዎች እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ህትመት ውጤቶች፣የፅዳት እቃዎች፣የቋሚ እና አላቂ የመረጃ ቴክኖሎጂ እቃዎች፣ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዥ፣ለተሽከርካሪዎችና ሌሎች መጓጓዣዎች እድሳት ጥገናና ጌጣጌጥ ግዥ ለፕላን፣ለማሽነሪ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና፣ህንፃና ቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳት እና ጥገና፣የመስተንግዶ ግብአት (ቆሎና ውሀ)፣ለህንፃ እና ለቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዣ(ቋሚ እቃዎች መግዣ)፣ልዩ ልዩ እቃዎች (አበባ እና አበባ ማስቀመጫ እንዲሁም ሌሎች) በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጸውን መስፈርት የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤
  2. የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (TIN) ያላቸው መሆኑን፤
  3. ገንዘብ ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና መረጃ ያላቸው፤
  4. ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምሥክር ወረቀት ከሰነዳቸው ጋር አያይዘው የሚያቀርቡ፤
  5. በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ ከሆኑ ከአደራጀው አካል የድጋፍ ደብዳቤ፤
  6. የጨረታ ማስከበሪያ መጠን፡- የደንብ ልብስ (ሎት1) 7,000.00፤ለአላቂ የጽህፈት እቃዎች (ሎት2) ብር 10,000.00፤ ለህትመት ውጤቶች (ሎት3) ብር 26,000.00፤ለጽዳት እቃዎች (ሎት4) ብር 3,000.00፤የመስተንግዶ ግብአት (ቆሎና ውሃ) ፤ (ሎት5) ብር 6,000.00፤ ልዩ ልዩ መሳሪያዎች (ሎት6) ብር 3,000.00፤ ለተሽከርካሪዎችና ሌሎች መጓጓዣዎች እድሳት ጥገናና ጌጣጌጥ ግዥ (ሎት7) ብር 8,000.00፤ ለህንጻ እና ለቁሳቁስ መገጣጠሚያዎች ዕቃ ግዥ (ሎት8) ብር6000.00፤ ለፎቶ ኮፒና ፕሪንተር እድሳትና ጥገና አገልግሎት እንዲሁም መለዋወጫ ዕቃዎች ለፕላን፣ለማሽነሪ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና፤ (ሎት9) ብር 7,000.00፤ ለፕላን፣ለማሽነሪ እና መሳሪያ ግዥ (ሎት10) ብር 10,000.00 ፤ለህንፃ፣ለቁሳቁስ ለተገጣጣሚዎች መግዣ (ቋሚ እቃዎች መግዣ) (ሎት11) ብር 5,000.00፤ልዩ ልዩ እቃዎች (አበባና አበባ ማስቀመጫ እንዲሁም ሌሎች) (ሎት12) ብር 3,000.00 በባንክ በተመሰከረለት (CP.O) ብቻ መያዝ አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ሎቶች የእቃው ናሙና ወይም ሳምፕል በድርጅቱ በተረጋገጠ ማህተም እና ፊርማ ከጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት በፊት ለግዥ ክፍል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ሳምፕል ሲወዳደር ካሳየው ሳምፕል ውጪ ካመጣ የመቀየር ግዴታ አለበት፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 400 (አራት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀን ስቴድየም አካባቢ ይሓ ሲቲ ሴንተር ህንፃ 3ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤታችን ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 303 መግዛት ይችላሉ፡፡
  9. ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የቴክኒክ ፕሮፖዛል "አንድ ኦርጅናል ኮፒ" እና የፋይናንሻል ዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር "አንድ ኦርጅናል ኮፒ የድርጅቱ ስም አድራሻ እና ማህተም እንዲሁም የሚጫረቱበትን የጨረታ ዓይነት ሎት በመፃፍ እና በየሎቱ በመለየት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ11ኛ ቀን ጥዋት 3:00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት ጥዋት 3:30 ሰዓት 6ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 604 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ በጨረታው መከፈቻ ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  10. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን የእቃው ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት (CPO) በማስያዝ ከመስሪያ ቤቱ ጋር ውል በመፈፀም አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት በማምጣት ቅ/ጽ/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
  11. ለጨረታ ከቀረቡት ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ እስከ 20% /ሃያ ፐርሰንት/ ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ተ.እ.ታ (ቫት) ጨምሮ ወይም ተ.እ.ታ (ቫት) በፊት መሆኑን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡ያልተገለፀ ከሆነ ተ.እ.ታ (ቫት) ጨምሮ እንደሆነ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡
  13. ተጫራቾች በጨረታው ሰነዱ የተገለፀው የመጫረቻ ሰነድ ማቅረቢያ የመጨረሻ ጊዜ ካለፈ በኋላ ወይም በጨረታው ሰነዱ በተገለፀው የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ውስጥ ራሱን ከጨረታ ካገለለ እና በጨረታው አሸናፊነቱ ከተገለፀ በሂላ ከተገለፀላቸው ቀን ቀርበው ውል ካልፈፀሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
  14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115581772/0115580505 መጠየቅ ይቻላል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ
የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa No. 2 Medium Taxpayers Office seeks suppliers for various goods and services in 12 lots: uniforms, stationery, printing, cleaning supplies, IT equipment, vehicle and machinery repair, building materials, and flowers. Bidders need a renewed license, TIN, VAT registration, and must submit samples.
Save Tender