የCCTV ካሜራ ከነ ሙሉ ዕቃና ኢንስታሌሽን እና የጣት አሻራ ማሽን ግዥ (02/19) - የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባለዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል
የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባላዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/19
በሲዳማ ብ/ክ/መ/ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባለዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት ህጋዊ ዕውቅና ካላቸው ድርጅቶች ከታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- LOT 1. CCTV Camera ከነ ሙሉ ዕቃና ኢንስታሌሽን
- LOV 2. ጣት አሻራ ማሽን
በመሆኑም በንግድ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ወረቀት የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለመጫረት የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ገንዘብ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን የተጫራቾች መመሪያና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከማዕከሉ ግገር ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ /ፕሮፎርማ/ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ የቴክኒካል እና የፋይናንሻል ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እያዳንዳቸው በተለያየ ፖስታ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እና CPO ቴክኒካል ዶኩሜንት ውስጥ በማድረግ አጠቃላዩን በአንድ ፖስታ በማሸግ በማዕከሉ በማዕከሉ ግገር ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- የጨረታውን ሳጥን የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛ ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 9፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት በማዕከሉ የግገር ፋይ/ንብ/አስ/ቢሮ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን ሳጥኑን የማሸጉም ሆነ የመክፈቱ ሥነ-ሥርዓት የሚከናወነው በቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓትና ሁኔታ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጊዜ ወይም በቦታው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያስተጓጉልም፡፡
ማዕከሉ ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር
0462129501/ 0462129504 ይደውሉ፡፡
የሀዋሳ ዳልጋ ከብት አባለዘር ማምረቻ፣ ማቀነባበሪያና ማሰራጫ ማዕከል /ሀዋሳ/
✨ messages.ai_summary
Hawassa Dilla Livestock Breeding, Processing and Distribution Center seeks to procure CCTV cameras with full equipment and installation, and a fingerprint machine, through open tender. Eligible bidders must have a renewed trade license, tax payment proof, taxpayer ID, and supplier registration certificate.
