Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
  • Address Addis Ababa Ethiopiaq, Phone: +251112730852
  • Website
  • Deadline10 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን (CPO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • opening dateህዳር 1 ቀን 2019 ዓ/ም (ምዝገባ እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ)
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Shares And Others Foreclosure

በአልፋቤት ት/ቤት ኃ/የተ/የግ/ማ 500 አክሲዮኖች የሐራጅ ሽያጭ - የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍርድ ባለመብት አየለ ፍስሀ እና በፍርድ ባለእዳ አማኑኤል ገ/ጻድቅ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 17761 በቀን 22/9/2017 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.19156 በቀን 29/11/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በአልፋቤት ት/ቤት ኃ /የተ/የግ/ማህበር በአቶ አማኑኤል ገ/ጻድቅ ያላቸው የአክሲዮን ብዛት 500 (አምስት መቶ) የአንድ አክሲዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) አጠቃላይ የአክሲዮን ዋጋ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ህዳር 1 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡

የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡ የሐራጅ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡

በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
A court-ordered auction of 500 shares in Alfabet School Association, held by the Federal Courts Execution Office. Bidders must deposit a CPO for one-quarter of the starting estimate; no more, no less. The buyer pays transaction tax. The winning bidder must deposit the full amount in 15 days.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender