በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት በተያዘው በጀት ዓመት የተለያየ አይነት ያገለገሉ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Ethiopian Electric Utility South Addis Ababa Region
የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን የተለያየ አይነት ያገለገሉ ንብረቶችን ለመሸጥ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ደ/አ/አ/ሪ/ብ/ግ/ጨ/001/2019
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት በተያዘው በጀት ዓመት የተለያየ አይነት ያገለገሉ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም
| ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት | ሎት | የሚገኙበት ቦታ | የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) | የጨረታው መዝጊያ ቀን | የጨረታው መክፈቻ ቀን |
| 1 | የተለያየ መጠን ያላቸው ብረታ ብረቶች | ሎት-1 | ጎፋ/ኮዬ ፕሮጀክት/ጎተራ እቃ ግምጃ ቤት | 120,000.00 | ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 | ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 |
| 2 | የተቆራረጡ የአልሙኒየም ሽቦ AAC & ABC | ሎት-1 | ||||
| 3 | የተለያዩ መጠን ያላቸው ኮፐር ኬብል | ሎት-1 | ||||
| 4 | የተለያዩ መጠን ያላቸው ጎማዎች | ሎት-1 | ||||
| 5 | የዘይት ብረት በርሜሎች | ሎት-1 | ||||
| 6 | የእንጨት ምሰሶ | ሎት-1 | ||||
| 7 | ያገለገሉ ጠረጴዛ ወንበሮች | ሎት-1 | ||||
| 9 | ያገለገሉ አሮጌ የተለያየ መጠን ትራንስፎርመሮች | ሎት -2 | ጎፋ እቃ ግምጃ ቤት | 150,000.00 | ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 | ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 |
በዚህ ጨረታ ላይ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የሚስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ EEU-South AddisAbaba Region customer contribution አካውንት ቁጥር 1000173799946 ገቢ በማድረግ የባንክ ስሊፕ በመያዝ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይ ቼይን፣ግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ EEU South Addis Abeba Region ተከፋይ የሚሆን ለሎት 1 ብር 120,000.00/አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 2 150,000.00/አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ተጫራቾች የከፈሉበትን ማስረጃ በመያዝ ከቢሮው ጋር በመነጋገር እቃዎቹን ባሉበት ቦታ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ላይ የሎት ቁጥሩና በግልጽ በመጻፍ ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በማድረግ እንዲሁም ሲፒኦ/CPO/ ኦርጅናል ሰነድ ውስጥ በመክተት በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በማድረግ እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ የቀድሞ ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ማክቤንዝ ህንጻ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ሰፕላይቼይን ግዥ ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-114705377 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን
✨ messages.ai_summary
Ethiopian Electric Utility South Addis Ababa Region seeks to sell various used property via open bid, including assorted metal, cut aluminum wire, copper cables, tires, oil drums, wooden poles, used tables/chairs, and old transformers. Bidders must be tax-compliant, licensed, and VAT-registered.
