Tender Detail

Tender Details

  • Company Hibret Bank S.C (ሕብረት ባንክ አ.ማ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251114655222
  • Websitehttps://www.hibretbank.com.et/
  • Deadline17 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ::
  • opening dateህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከ8:00 እስከ 9:00 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Automotive Materials

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል::

Hibret Bank S.C (ሕብረት ባንክ አ.ማ)


የሐራጅ ማስታወቂያ

ሕብረት ባንክ አ.ማ. በቅርንጫፉ በኩል ለሰጠዉ ብድር በመያዣነት የያዘዉን ከዚህ በታች የተመለከተውን ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልጽ ሐራጅ (ጨረታ) አወዳድሮ ይሸጣል::

ተ.ቁ.የተበዳሪው ስምአስያዥአበዳሪው ቅርንጫፍየተሽከርካሪው አይነትየሰሌዳ ቁጥርየሞተር ቁጥርየሻንሲ ቁጥርየስሪት ዘመንየሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር (ቫትን ሳይጨምር)ሐራጅ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት
1ኤልሳቤጥ ባለው ካሳመላኩ ባለው ካሳየሺ ደበሌሱዙኪ ዲዛየር አውቶሞቢልአአ-02-B82171K12MN4716628MA3ZF6C11MA7870342021 እ.ኤ.አ3,130,434.78ህዳር 08 ቀን 2019 ዓ.ም ከ8:00 እስከ 9:00 ሰዓት

የሐራጅ ደንቦች፡-

  1. ተጫራቾች የሐራጁን መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ በሕብረት ባንክ አ.ማ. (Hibret Bank S.C) ስም የተሰራ የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ.) ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ:: ከባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ውጭ የሚቀርብ የጨረታ ማስያዣ ተቀባይነት የለውም::
  2. ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከብድር ክትትል እና እዳ ማሰባሰብ መምሪያ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ዕለት ሶስት ቀናት በፊት መጎብኘት ይችላል::
  3. በሐራጅ ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ተበዳሪ እና አስያዥ ብቻ ናቸው:: ተጫራቾች በሐራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ መያዝ ይገባቸዋል:: ተጫራቾች የሕግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ሕጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሐራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ሰው ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ፅ/ቤት ወይም በተመሳሳይ አካል የፀደቀ መመስረቻ ፅሁፍ (የመተዳደሪያ ደንብ)፣ቃለ ጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት::
  4. የተጠቀሱት ንብረቶች ሐራጁ የሚካሄደው የሕብረት ባንክ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት ሕንፃ (ሕብር ታወር) 26ኛ ፎቅ የሕግ አገልግሎት መምሪያ ባለው የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ነው::
  5. የተጫራቾች ምዝገባ ከሐራጁ መዝጊያ ሰዓት ሰላሳ ደቂቃ በፊት ይደረጋል::
  6. ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል:: ከፍተኛ ዋጋ ለሰጠ ተጫራች ደግሞ ያቀረበውን ዋጋ ባንኩ ሲቀበለው ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ እንዲከፍል የሚገልፅ ደብዳቤ የሚሰጠው ሲሆን በዚህ ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል::
  7. ከፍ ሲል የተጠቀሰውን ንብረት ለሚገዙና የባንኩን የብድር ፖሊሲ እና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟሉ ተጫራቾች በሚሰጠው ከፍተኛ ዋጋ ላይ ባንኩ እስከ 50%(ሃምሳ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል::
  8. ተጨማሪ እሴት ታክስ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ የታክስና ግብር የስም ማዛወሪያ ጭምር የጨረታዉ አሸናፊ (ገዥዉ) ይከፍላል::
  9. ባንኩ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  10. ለተጨማሪ መረጃ ብድር ክትትል እና እዳ ማሰባሰብ መምሪያ በስልክ ቁጥር 0114706380/0114666593 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል::
✨ messages.ai_summary
Hibret Bank auctions a foreclosed Suzuki Dzire automobile held as loan collateral. Bidders must bring an ID; legal entities need their main registration certificate and a document certified by the documents registration office showing their representative's authority.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender