ድርጅታችን ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል ማህበር የኮንስትራክሽን ዕቃዎች, ያገለገሉ ሚክሰር ቫይብሬተር, አዲስ መለዋወጫ ዕቃዎች, አዳዲስ የባንባ ዕቃዎች, በሚገኙበት ቦታ ገላን ከተማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ተክኖሎጂ አስቱ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
YOTEK Construction Plc
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ.የተ.የግል ማህበር የኮንስትራክሽን ዕቃዎች, ያገለገሉ ሚክሰር ቫይብሬተር, አዲስ መለዋወጫ ዕቃዎች, አዳዲስ የባንባ ዕቃዎች, በሚገኙበት ቦታ ገላን ከተማ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ተክኖሎጂ አስቱ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ንብረት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከድርጅታችን ዋና ቢሮ 2ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 300 በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኘው ገላን ከተማና አዲስ አበባ ሳይንስና ተክኖሎጂ አስቱ ቀርበው መመልከት ይችላሉ::
- ማንኛውም በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች የተጠቀሱት ንብረቶች የጨረታው ማስከበሪያ (Bid Bond) ከምታቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ ከዋናው ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ዶክመንት ዉስጥ በተዘጋጀዉ የማጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ዉስጥ አስገብተዉ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 22/02/2019 ዓ/ም ጀምሮ ባሉት ቅዳሜን ጨምሮ 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ዉስጥ ዋናዉ መ/ቤት መግቢያ ላይ ባለዉ የእንግዳ መቀበያ አጠገብ በተቀመጠዉ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
- ጨረታዉ በቀን 30/02/2019 ዓ/ም ሰኞ 11:00 ሰአት ይዘጋል::
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅታችን ዋና መ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በቀን 01/03/2019 ዓ/ም ማክሰኞ ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይከፈታል:: ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ካልተገኙ ጨረታው በጨረታ ኮሚቴና ታዛቢ ባሉበት የሚከፈት መሆኑን እናሳውቃለን::
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ተ/እ/ታ /VAT/ ያካተተ መሆን ይኖርበታል::
- ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ካቀረቡት ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ::
- የመጫረቻ ዋጋ ቅፅ ላይ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እና አሻሚነት ያለው የቁጥር አፃፃፍ ተቀባይነት የለውም::
- የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 3 ቀናት ውስጥ ክፍያውን ሙሉ በሙሉ ከፍለው ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው አሸናፊዎች ክፍያ ከፈፀሙ በ10 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ትራንስፖርትና ወጪ ንብረቱን ሙሉ በሙሉ ማንሳት ይኖርባቸዋል::
- የጨረታው አሸናፊዎች ክፍያ በተቀመጠው በ3 ቀናት የጊዜ ገደብ ካልከፈለ ጨረታው ውድቅ ሆኖ ለጨረታው ያስያዙት /bid bond/ ተመላሽ አይደረግም::
- በጨረታው ተሳታፊ ሆነው ጨረታውን ላላሸነፉ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት (Bid Bond) ተመላሽ ይደረጋል::
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለተጨማሪ መረጃ
አድራሻ:- ዮቴክ ኮንስትራክሽን ኃ. የተ. የግል ማህበር
ቫቲካን ፊት ለፊት ያለው መርየም ህንፃ እንገኛለን
የስልክ ቁጥር 0115573196/0115573198
ፋክስ 0115573187/0115573197
ኢ-ሜይል yotekconplc@gmail.com
አዲስ አበባ
✨ messages.ai_summary
Sale by Yotek Construction of construction materials, used mixers and vibrators, new spare parts and new pump items, held at its Gelan town and Addis Ababa Science and Technology University sites, sold as is. Bidders' prices must include VAT.
