Tender Detail

Tender Details

  • Company በልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የእናት ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና ካራማራ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address , Phone: 0112300115---0111230120
  • Website
  • Deadline15 Oct 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200
  • Bid Securityበሎት: ከብር 1,000 እስከ 3,500 (CPO)
  • opening dateበማግስቱ 4:30 በት/ቤቱ ቤተ መፅሀፍት ይከፈታል
  • Categories Maintenance And Repair , Stationery Materials , Cloth And Shoes

በልደታ ክ/ከተማ የእናት ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና ካራማራ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የደንብ ልብሶች፣ አላቂ የቢሮ እና የትምህርት እቃዎች፣ ህትመት፣ የፅዳት እቃዎች፣ ፕላንትና ማሽነሪ፣ የህንፃ እድሳትና ጥገና እና ሌሎች ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ መፈጸም ይፈልጋል

በልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የእናት ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና ካራማራ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የእናት ኢትዮጵያ የመጀ/ደ/ት/ቤት እና ካራማራ ቅድመ አንደኛደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ/ም በግልጽ ጨረታ ግዥዎችን መፈጸም ይፈልጋል፡፡

ሎት የግዥ አይነት የጨረታ ማስከበርያ በብር መጠን
ሎት 1 የደንብ ልብሶች 2,000
ሎት 2 አላቂ የቢሮ እቃዎች 2,000
ሎት 3 ህትመት 1,000
ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች 1,000
ሎት 5 ሌሎች አላቂ የፅዳት እቃዎች 1,000
ሎት 6 ልዩ ልዩ መሳርያዎች 2,000
ሎት 7 ፕላንትና ማሽነሪ መግዣ 3,500
ሎት 8 የህንፃና ቁሳቁስ መግዣ 1,500
ሎት 9 የሰራተኛ የደንብ ልብስ ስፌት እቃዎች መግዣ 1,500
ሎት 10 አላቂ የህክምና እቃ መግዣ 1,000
ሎት 11 ህንፃና ቁሳቁስ እድሳትና ጥገና 3,500

ለጨረታው የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

  1. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የከፈለ እና የዕቃ አቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው እና የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
  2. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በእናት ኢትዮጵያ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዥና ን/አስ/ደጋፊ የስራ ሂደት በግንባር በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ግዥ ክፍል ቢሮ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ11:30 ሰዓት ታሽጎ በማግስቱ 4:30 በት/ቤቱ ቤተ መፅሀፍት ይከፈታል፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና (sample) ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የተሟላ ፍላጎት መግለጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸው እቃዎች ለእያንዳንዱ የሚያቀርቡት ዋጋ ከቫቱ መሆን አለበት፡፡
  8. የዘገየ ጨረታና ስርዝ ድልዝ ያለበት ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  9. አማራጭ ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ናሙና ማቅረብ የማይቻልባቸው ትልልቅ እቃዎች ፍላጎት መግለጫ( specification) ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
  13. ናሙናዎች በሙሉ መቅረብ የሚችሉት ለግዢ ክፍል ብቻ በመረካከቢያ ቅፅ ላይ ተሞልቶ መሆን አለበት፡፡

አድራሻችን፤- አብነት በሞላ ማሩ ወደ ጌጃ ቃለ ህይወት በሚወስደው መንገድ ገባ ብለው ያገኙናል፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112300115---0111230120

በልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የእናት ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና ካራማራ ቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
Open tender by Lideta Sub-City Education Office for Enat Ethiopia Primary and Karamara Pre-Primary Schools covering uniforms, consumable office and educational materials, printing, cleaning supplies, equipment, plant and machinery, building materials, renovation and maintenance. Bidders need renewed license, tax clearance, supplier registration, VAT registration, and a bank-verified CPO.
Save Tender