Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
  • Address በቅሎ ቤት ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ዳቤ ቤኛ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-4-70-52-41
  • Website
  • Deadline12 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityበሎት: ከብር 2,000 እስከ 18,700 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበ11ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት በቅ/ጽ/ቤቱ አንደኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ
  • Categories Printing And Publishing , Computer Laptop And Accessories , Stationery Materials

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት


የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

01/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የደንብ ልብስ ፣ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የህትመት ውጤቶች፣ ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣ የመረጃ ቴክኖሎጂ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የመፀዳጃ ቤት ጥገና ዕቃዎች፣ የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች እና የመረጃ ቴክኖሎጂ ዕቃዎች የጥገና እና የሰርቪስ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውን ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና Tin ሰርተፍኬት ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እና መረጃ ያላቸው፡፡
  3. ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ መ/ቤት ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በየሎቱ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት አንድ የደንብ ልብስ ብር 3,200.00 (ሶስት ሺህ ሁለት መቶ ብር)፣ ለሎት ሁለት አላቂ የጽህፈት ዕቃዎች 13,000.00 (አስራ ሶስት ሺህ ብር)፣ ለሎት ሦስት የህትመት ውጤቶች ብር 9,000 (ዘጠኝ ሺህ ብር)፣ ለሎት አራት ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች 7,500.00 (ሰባት ሺህ አምስት መቶ ብር)፣ ለሎት አምስት የመረጃ ቴክኖሎጂ ዕቃዎች18,700.00 (አስራ ስምንት ሺህ ሰባት መቶ) ብር ብቻ ሎት ስድስት የፅዳት ዕቃዎች ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)፣ ሎት ሰባት የመፀዳጃ ቤት የጥገና ዕቃዎች 4,800.00 (አራት ሺህ ስምንት መቶ ብር)፣ሎት ስምንት የመኪና ጌጣጌጥ ዕቃዎች 5,900.00 (አምስት ሺህ ዘጠኝ መቶ) ብር፣ሎት ዘጠኝ የመረጃ ቴክኖሎጂ ዕቃዎች የጥገና እና ሰርቪስ አገልግሎት ግዥ 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር) ሲፒዮ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በቅሎ ቤት (ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት) ዳቢ ቤቸ ታወር 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የቅ/ጽ/ቤታችን ግዥና ፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒውን ለብቻ በማድረግ ዘወትር በሥራ ቀንና ሰዓት ቅዳሜን ጨምሮ ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቅ/ጽ/ቤቱ አንደኛ ፎቅ ግዥና ፋይናንስ ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  8. የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ላይ ካልዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን ይከፈታል፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 0114-70 52 41 /0114-70-58-17

አድራሻ፡- በቅሎ ቤት ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ዳቢ ቤቸ ህንፃ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ ከፍተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Addis Ababa Revenue Bureau's Large Taxpayers Office seeks legally licensed bidders to supply uniforms, consumable and fixed office supplies, printed materials, IT equipment, cleaning and toilet maintenance items, vehicle accessories, and IT maintenance services. Bidders need a renewed trade license, TIN, MoFED supplier registration, tax clearance, and VAT registration.
Save Tender