በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የምዕራፍ አጠቃላይ /2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከመደበኛ በጀት እና ከውስጥገቢ በጀት በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የትምህርት መገልገያ እና የቢሮ መሳሪያዎችን የጥገና ስራዎችን በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የምዕራፍ አጠቃላይ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02 /2019
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በጉለሌ ክ/ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ስር የሚገኘው የምዕራፍ አጠቃላይ /2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ከመደበኛ በጀት እና ከውስጥገቢ በጀት በመንግስት ግዥ መመሪያ መሰረት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውል የትምህርት መገልገያ እና የቢሮ መሳሪያዎችን የጥገና ስራዎችን በ2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከ የምዕራፍ አጠቃላይ/2ኛ/ደረጃ ት/ቤት ግዢ ቢሮ ቁጥር 12 መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
| ተ.ቁ | የእቃው አይነት | ሎት | የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
| 1 | የፅህፈት እና የቢሮ እቃዎች | 1 | 2’285 |
| 2 | የፅዳት እቃዎች | 2 | 1’040 |
| 3 | ደንብ ልብስ | 3 | 6,750 |
| 4 | የደንብ ልብስ ስፌት | 4 | 6,750 |
| 5 | ለትምህርት ዕቃዎች | 5 | 7,500 |
| 6 | ለፕላንት ለማሽነሪ መሳሪያ መግዣ(የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች) | 6 | 19,500 |
| 7 | የህክምና እቃዎች (የቀይ መስቀል እቃዎች) | 7 | 500 |
| 8 | ለፕላንት ህንፃ እና ተገጣጣሚ መግዣ | 8 | 6,000 |
| 9 | የግብርና ዕቃዎች | 9 | 50 |
| 10 | ለምርምር እና ለልማት አላቂ እቃ | 10 | 250 |
| 11 | የኤሌክትሮኒክስ ማሽን ጥገናዎች | 11 | 590 |
| 12 | የተለያዩ የጥገና ስራዎች | 12 | 3,825 |
| 13 | ዉሃ እና ቀለም | 13 | 604 |
| 14 | የህትመት ዉጤቶች | 14 | 647 |
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል እና የዘመኑ ግብር የከፈለ፡፡
- በዘርፉ የተሰማሩበት ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- አቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በግልፅ ማስፈር እናመጨረሻ ቦታ ላይ ፊርማ እና ማህተም በመምታት በ1 ኦርጅናል እና 1 ኮፒ አሽገው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- 6. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች ከአጠቃላይ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውል ማስከበሪያ በማስያዝ እና የግዥ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርባቸዋል ፡፡
- አሸናፊው ድርጅት የትራንስፖርት ወጭ በራሳቸው እስከ ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- 8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታ የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በወጣበት 10ኛው ቀን 11:00 ሰዓት ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 በት/ቤቱ ግዥ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል፡፡
- እያንዳንዱ ተጫራች የዕቃዎችን ናሙና /ሳምፕል/ የጨረታውሰነድ ሲገባ (ጨረታዉ ከመከፈቱ በፊት) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የውል ማስከበሪያም ሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በጥሬ ገንዘብ የማንቀበል መሆኑን እየገለፅን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስገባት ይኖርባቸዋል።ነገር ግን ለሎት 9እና 10 በጥሬ ገንዘብ ማስያዥ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ትምህርት ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የእቃዉን መጠን ከውል በፊት 20% መጨመር እና 20% የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች በጥቃቅን እና አነስተኛ ፍቃድ የምትወዳደሩ ከሆነ አምራቾች ባመረቱት ምርት (ተጨማሪ እሴት)ያላቸው መሆን አለባቸው።በዚሁ መሰረት ልዩ አስተያየት የሚደረግላቸው መሆኑን እየገለፅን ከአደራጅ ተቋም ይህን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ እንድታቀርቡ እንጠይቃለን፡፡
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- አዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 እንበሳ ጋራዥ በስተጀርባ ወይም ከዊንጌት ወደ አዲሱ ገበያ በሚወስደው መንገድ በስተቀኝ ከፖሊስ እስቴሽን ከፍ ብሎ የምዕራፍ አጠቃላይ /2ኛ ደረጃ ት/ቤትወይም ከአዲሱ ገበያ ዊንጌት በሚወስደዉ መንገድ በስተግራ በኩል ዜብራ መንገድ ተሻግሮ ከአገሬ ቱሉ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ዝቅ ብሎ ባለዉ ቀጭን መንገድ ገባ ብሎ ወደቀኝ ታጥፎ የምዕራፍ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በሮ ቁጥር 12፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-2595671
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የምዕራፍ አጠቃላይ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት
✨ messages.ai_summary
The school seeks maintenance services for educational and office equipment, plus supplies including stationery, cleaning materials, uniforms, electronics, medical, agricultural, printing and construction items, across 14 lots. Bidders must hold a valid trade licence, tax clearance, supplier registration and VAT certificate, and submit samples.
