Tender Detail

Tender Details

  • Company በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የአድዋ በር የመ/ደ/ት/ቤት
  • Address የካ ክ/ከተማ ወርዳ 07 ጽ/ቤት ጀርባ የቀድሞ 09 መብራት ኃይል አጠገብ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-6-36-65-55
  • Website
  • Deadline14 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት 200.00 (ሁለትመቶ ብር)
  • Bid Securityበየሎቱ ከ200.00 (ሁለት መቶ ብር) እስከ 8,383.20 (ስምንት ሺ ሶስት መቶ ሰማንያ ሶስት ብር ከ20 ሳንቲም)
  • opening dateበዚያው ቀን በ4፡30
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment , Stationery Materials , Cloth And Shoes

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የዓድዋ በር የመ/ደ/ት/ቤት አ01/2019 በ2019 ዓ.ም በግልፅ ጨረታ የደንብ ልብስ፣ የቢሮና የትምህርት ዕቃዎች፣ የጥገና ዕቃዎች፣ የማሽነሪ ጥገና፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ ቋሚ ዕቃዎች፣ የምግብ አቅርቦት፣ ህትመት፣ የሕክምና እና የላብራቶሪ እቃዎች (10 ሎቶች) አወዳድሮ ግዢ መፈፀም ይፈልጋል።

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የአድዋ በር የመ/ደ/ት/ቤት


የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ01/2019ዓ.ም

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የዓድዋ በር የመ/ደ/ት/ቤት 2019 ዓ.ም ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተ.ቁ ሎት የጨረታው አይነት   የጨረታው ማስከበሪያ የገንዘብ መጠን
1 ሎት 001 የደንብ ልብስ እና የስፖርት መምህራን ትጥቅ ናሙና የሚቀርብበት 8307.61
2 ሎት 002 አላቂ የቢሮ እና የትምህርት ዕቃዎች (የፅሕፈት መሣሪያዎች) ናሙና የሚቀርብበት 8000.00
3 ሎት 003 የጥገና ዕቃዎች (የሕንፃ መሣሪያዎች) ናሙና የሚቀርብበት 6000.00
4 ሎት 004 የማሽነሪ ጥገና ሥራ (ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒ ) የሥራውን ሰነድ በመግዛት 1000.00
5 ሎት 005 የንፅሕና መጠበቂያ ዕቃዎች (የፅዳት እቃዎች) ናሙና የሚቀርብበት 8383.20
6 ሎት 006 የቢሮ ማሽነሪ (ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ወንበር፣ ጠረጴዛ ወዘተ) ቋሚ ዕቃዎች በፎቶ ናሙና የሚቀርብበት 7500.00
7 ሎት 007 የት/ቤቱ ለሚሰጠው ስልጠና የውሃ፣ ቆሎ፣ ኩኪስ እና የመሳሰሉትን አቅርቦት ለዓመት በውል ማቅረብ ሰነድ በመወሰድ 5000.00
8 ሎት 008 የህትመት ሥራ መጥተው ሥራውን በማየት 1000.00
9 ሎት 009 የሕክምና እቃ በናሙና የሚቀርብበት 200.00
10 ሎት 010 የላብራቶሪ እቃዎች በናሙና የሚቀርብበት 8000.00

ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም በፌዴራል የመንግሥት ግዥ አስተዳደር የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ለመመዝገብ የምስክር ወረቀት፣ የቫት ሰርተፍኬት፣ የግብር መከፈያ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚጫረቱበት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር /200/ ሁለት መቶ ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት የመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ት/ቤቱ ፋይናንስ የሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይችላል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚጫረቱበት አይነት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በዓድዋ በር የመ/ደ/ት/ቤት ስም በየሎቱ በተዘረዘረውና በተቀመጠው የገንዘብ መጠን መሠረት ነው።
  4. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚጫረቱበት ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በመቅረብ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ኦርጅናል እና ኮፒውን ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
  6. አሸናፊ ድርጅት ለሚወዳደሩበት ለእያንዳንዱ እቃ ናሙና ማቅረብ የሚጠበቅበት ሲሆን ናሙና ያልቀረበበት እቃ ከውድድር ውጪ የሚሆን ስለሚሆን በርክክብ ቀን ባቀረበው ናሙና መሰረት ገቢ የሚደረግ ሲሆን ካላቀረበ ያስያዘው CPO ለመንግሥት ገቢ ይሆናል።
  7. በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መጠን በላይም ሆነ በታች በተመደበለት በጀት ጋር አጣጥሞ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀን ተዘግቶ በቀጣዩ የሥራ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ውስጥ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ላይ በግልፅ ይከፈታል።
  9. ጨረታው ተከፍቶ አሸናፊው ድርጅት ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ውል በሚዋዋልበት ጊዜ ባሸነፈበት ዕቃዎች መጠን 10% CPO ወይም የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  10. ለማሽነሪ ጥገና የምትወዳደሩ ተወዳዳሪዎች ት/ቤቱ ለ1ዓመት በውል እንደምትሠሩለት ውል በመግባት ይሆናል ስለዚህ ለጥገና በምትወዳደሩበት ጊዜ የምትሰጡት ዋጋ ዓመታዊ ዋጋ መሆን ይጠበቅበታል የጥገና ሥራው ተቀያሪ ዕቃን አያካትትም።
  11. የሀገር ውስጥ ተጫራቾች ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን ጨረታ ላይ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ ክሊራንስ (ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው)።
  12. ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ተጫራች በእያንዳንዱ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም መምታት ይኖርበታል።

አድራሻ፡- የካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ጽ/ቤት ጀርባ የቀድሞ 09 መብራት ኃይል አጠገብ

ለበለጠ መረጃ፡- 0116-36-65-55

በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 07 የዓድዋ በር የመ/ደ/ት/ቤት

✨ messages.ai_summary
The school seeks suppliers for uniforms, office and educational materials, maintenance and cleaning supplies, machinery maintenance, durable goods, annual food supply, printing, and medical/laboratory items across 10 lots. Bidders need a renewed business license, tax clearance, VAT certificate, and registration certificate. Samples are required for most lots.
Save Tender