Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama National Regional State Revenue Authority (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን)
  • Address ሀዋሳ ከአሮጌ መናኸሪያ ጀርባ 300 ሜትር ገባ ብሎ ፡ ሀዋሳ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462125156
  • Website
  • Deadline16 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200
  • Bid Securityሎት 1 = 30,000, ሎት 2 = 10,000 ሎት 3 = 25,000, ሎት 4 = 5,000, ሎት 5 = 10,000 እና ሎት 6 = 25,000 በባንክ በተመሰከረ CPO
  • opening date16ኛው ቀን ከጧቱ 4:30 በክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  • Categories Maintenance And Repair , Office And Home Furniture , Electronics Materials

የኤሌክትሮኒክስ፣ እስቴሽነሪ፣ ፈርኒቸር፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ ሞተርሳይክል ግዥ እና የመኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ - ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን

Sidama National Regional State Revenue Authority (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን)


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን በ2019 በጀት ዓመት ሎት 1= ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ፣ ሎት 2= እስቴሽነሪ እና ሌሎች አላቂ እቃዎች ግዥ ፣ ሎት 3= ፈርኒቸር ዕቃ ግዥ፣ ሎት 4= የጽዳት ዕቃዎች፣ ሎት 5= ሞተርሳይክል ግዥ፣እና ሎት 6= የመኪና ጥገና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ ድርጅት በጨረታው እንዲሳተፍ እየጋበዝን በጨረታው ላይ ለመካፈል አቅራቢው ቀጥሎ የቀረቡት መመዘኛዎች ወይም መስፈርቶች ማሟላት አለበት፡፡

  1. በዘርፉ የታደሰ ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የአቅራቢዎች ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. ጨረታዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት ቀናት/ ተከታታይ የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡
  3. የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ የሚያመላክት የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የንግድ ፈቃዳቸውን በመያዝ ቀርበው ከቢሮ ቁጥር 06 በ200 መቶ ብር በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች ለውድድር ሲቀርቡ ለጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 = 30,000, ሎት 2 = 10,000 ሎት 3 = 25,000, ሎት 4 = 5,000, ሎት 5 = 10,000 እና ሎት 6 = 25,000 በባንክ በተመሰከረ CPO በፖስታ አሽገው ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ተቀባይነት የለውም፡፡
  5. ጨረታዉ 16ኛው ቀን ከጧቱ 4:00 ታሽጎ 4:30 በክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን ግዥ/ፋ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ቀኑ በዓል ወይም የእረፍት ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው በሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች የፋይናንሻል የቴክኒክ መገምገሚያ መስፈርት በመሙላትና በተለያየ ሁለት ኦርጅናል ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የፋይናንስ የቴክኒክ መሆኑን በመግለጽ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሰጡት ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ማካተት አለማካተቱን በፋይናንሻል ጨረታ ዋጋ ማቅረቢያው ላይ በግልጽ ማሳየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን አልወዳደርም ማለት አይችልም፡፡
  9. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉ በፅሁፍ ከተገለጸለት በኋላ በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ CPO በመያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡ ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይገባ/ ባይፈጸም/ የጨረታ አሸናፊነቱ ይሰረዛል፡፡
  10. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅትን ወክሎ ውሉን የሚፈርም የድርጅቱ ባለቤት ሳይሆን ቀርቶ ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውክልናና ኦርጅናልና የማይመለስ ኮፒ ይዞ መቅረብ አለበት፡፡
  11. ለጨረታው የውል ማስከበሪያ የተያያዘው ገንዘብ አሸናፊው ተጫራች ግዴታውን በሙሉ መሰረት ካልፈጸሙ በሙሉ ላይ በሚገልጸው ህግ መሰረት መ/ቤቱ ተፈፃሚ የማድረግ መብት አለው፡፡
  12. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዕቃ ወይም አገልግሎት የአያንዳንዱ ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት በፋይናንሻል በጨረታ ሰነዱ ሳይ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም /መሙያ/ ውስጥ ብቻ መሆን አለበት፡፡
  13. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነዉ፡፡

አድራሻ ፡ ሀዋሳ የዲሮ ደህዴን ጀርባ እንገኛለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0462125156 ይደውሉ፡፡

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ባለሥልጣን

✨ messages.ai_summary
The Sidama National Regional State Revenue Authority seeks suppliers for electronics, stationery and consumables, furniture, cleaning materials, motorcycles, and vehicle repair services via open tender. Eligible bidders must be licensed in the sector and provide tax identification, VAT registration, supplier registration certificates, and proof of current tax payment.
Save Tender