Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
  • Address በስልጤ ዞን ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 882 0005
  • Website
  • Deadline30 Sep 2026, 12:42 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200 (ሁለት መቶ) ብር
  • Bid Securityለሎት1 ብር 70,000 (ሰባ ሺህ) እና ለሎት2 ብር 20,000(ሃያ ሺህ) - ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንቲ
  • opening dateበ10ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ሰዓት ይከፈታል:: 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል::
  • Categories 3- Wheel Vehicle, Motorcycles And Bicycles , Geophysical instrument

ሞተር ሳይክሎች እና ቶታል እስቴሽን - የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2019 በጀት ዓመት ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ ሞተር ሳይክሎችን እና ቶታል እስቴሽን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::

በመሆኑም :-

  • ሎት 1 ሞተር ሳይክል
  • ሎት 2 ቶታል እስቴሽን
  • የዘመኑን የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል
  • የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
  • የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት1 ብር 70,000 (ሰባ ሺህ) እና ለሎት2 ብር 20,000(ሃያ ሺህ) ለየብቻ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
  • ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ለየብቻ ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናል እና 2ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ቴክኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል:: የጨረታ ሳጥኑ በ10ኛው ቀን በ8:00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ሰዓት መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል::

ማሳሰቢያ:-

ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ጥያቄው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል::

መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467710586

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Supply of motorcycles (Lot 1) and a total station (Lot 2) for sector offices in Silte Zone. Bidders must have a renewed business license, TIN, supplier registration certificate, and VAT registration. Financial and technical documents must be submitted separately in sealed envelopes.
Save Tender