ልዩ ልዩ የወረቀት ግብዓቶች (Yellow Bank Paper፣ White Wood Free Paper፣ Wood Free፣ Leather Board Paper) ግዥ - ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
Berhanena selam printing enterprise (ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 027/19
ድርጅታችን ለሥራ አገልግሎት የሚጠቀምባቸውን ልዩ ልዩ ግብዓቶች ማለትም Yellow Bank Paper 61x86cm 45gm ብዛት 1,500,000 ቅጠል፣ White Wood Free Paper 61x86cm 70gm ብዛት 1,300,000 ቅጠል፣ Wood Free 60gm 42cm ብዛት 100,000 ኪ.ግ፣ White Wood Free Paper 84cm 80gm ብዛት 200,000 ኪ.ግ እና Leather Board Paper 70x100cm 600gm ብዛት 3,000 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ወቅታዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የገንዘብ ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢዎች ምዝገባ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በድርጅቱ ዋና መ/ቤት (አራት ኪሎ) አዲሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው የዕለት ገንዘብ ተቀባይ የማይመለስ ብር 500.00 ከፍለው በመግዛት የፋይናንሺያል እና የቴክኒካል የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን ዋናውን እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት 6ኛ ፎቅ ነባሩ ህንፃ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው፡፡
ጨረታው በ17/2/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ የቴክኒካል መጫረቻ ሰነድ (ከላይ የተገለፁ ለቅድመ ግምገማ የሚያገለግሉ ዶክመንቶች የጨረታ ማስከበሪያ) ብቻ ከሰዓት 8:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ነባሩ ህንፃ 6ኛ ፎቅ በሚገኘው በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ይከፈታል፡፡ የፋይናንሻያል የመጫረቻ ሠነዶች የሚከፈቱት የቴክኒካል ሰነዳቸው ተቀባይነት ላገኙት ብቻ ነው፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም፡፡
ስልክ ቁጥር 011-1-55-52-30
ድረ ገፅ (www.ethbspe.org)
Berhanena selam printing enterprise
አዲስ አበባ
