Tender Detail

Tender Details

  • Company የጊምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ
  • Address ጊምቢ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 057-7-71-18-72
  • Website
  • Deadline08 Oct 2026, 3:00 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 100.00
  • Bid Securityከጨረታ ሠነድ ጋር ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 1% በተረጋገጠ ባንክ (CPO)
  • opening dateበ16ኛው ቀን በስድስት ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ9:00 ሰዓት
  • Categories Building Materials , Electrical And Electromechanical , Water Pipes And Fittings

የጊምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሚሰጠው ሥልጠና የሚውል የኤሌክትሪክ፣ የውሃ ቧንቧ እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የጊምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ


የጨረታ ማስታወቂያ

የጊምቢ ፖሊ ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለሚሰጠው ሥልጠና የሚውል የኤሌክትሪክ፣ የውሃ ቧንቧ እና የኮንስትራክሽን ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም የሚከተለውን የጨረታ መሥፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

  1. ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡ።
  3. የታክስ ከፋይነት /TIN/ የተመዘገቡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን ማስረጃ የሚያቀርቡ።
  4. ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 1% በተረጋገጠ ባንክ (CPO) ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 በመክፈል ከኮሌጁ ግዥ እና ፋይናንስ አስተዳደር ሥራ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች ሠነዱን ቀኑ ሲደርስ በጊምቢ ፖሊቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት በ16ኛው ቀን በስድስት ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ9 ሰዓት ተጫራቾቹ ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል።
  8. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ሲቀርቡ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ኮሌጁ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  9. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0577711872፣ 0577710005 በተንቀሳቃሽ ስልክ 0911916733 0919294017 ደውለው ሊረዱ ይችላሉ።

የጊምቢ ፖሊ‐ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ሥልጠና ኮሌጅ

✨ messages.ai_summary
Gimbi Polytechnic College seeks to procure electrical, water pipe, and construction materials for its training program. Eligible bidders must hold a valid trade license, provide tax payment and TIN/VAT registration evidence, and submit a 1% CPO bid security.
Save Tender