Tender Detail

Tender Details


የጽህፈት መሳሪያ፣ ፅዳት፣ ቋሚ እቃዎች፣ የህንፃ መሳሪያ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ጎሚስታና ጋራጅ ጥገና፣ ጎማና ባትሪ ግዥ (11 ሎት) - የደሴ ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የደሴ ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ እና በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 ዓ.ም በጀት አመት የተለያዩ ቋሚ እና አላቂ እቃዎች እንዲሁም የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የጎሚስታ ጥገና አገልግሎት ለማገኘት፡-ሎት፡1.አላቂ የጽህፈት መሳሪያ ሎት 2.የፅዳት እቃዎች ሎት፤3.ቋሚ እቃዎች ሎት፤4.የህንፃ መሳሪያሎት፤5.የከባድ እና የቀላል ተሽከርካሪዎች ጎሚስታ ሎት 6.የቀላል ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ሎት 7 የከባድ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ሎት፡8.ቢሾፍቱ የከተማ አውቶብስ መለዋወጫ ሎት፡9.የከባድ ተሽከርካሪዎች የጋራጅ ጥገና አገልግሎት ሎት 10. የቀላል ተሽከርካሪዎች የጋራጅ ጥገና አገልግሎት ሎት፡11 የከባድ እና የቀላል ተሽከርካሪዎች ጎማና ባትሪ በግልፅ ጨረታ በማወዳደር አሸናፊ በመለየት አመታዊ ውል ይዞ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለዚህ ከዚህ ባታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል፡፡

  1. በዘርፍ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ
  2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ እና የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት ማቅረብ የሚችል
  3. ግዥው ከ500000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ከፋይነት ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 300 ብር ከግዥ ፋይናንስ አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 18 ላይ በመምጣት ከ18/2/2019 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/2/2019 11፡30 ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥ ፋይናስ ቡድን አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ፡፡
  6. የሚገዙ እና የሚሰሩት አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን ከጨረታው ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝና ፍሉድ መደረግ የለበትም ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ድምር 2% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው እንዲሁም አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የውሉታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ደሴ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥና ፋይናንስ ቡድን አዲሱ ቢ.ሮ 3ኛ ፎቅ ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ30/2/2019 ዓ.ም 3፡30 ድረስ ሰነዱን በማስገባት ይታሸጋል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 30/2/2019 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥ አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ መከፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡
  11. ውድድሩ የሚካሄደው በጥቅል ድምር ወይም በሎት ድምር ውጤት ነው፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስ.ቁ 0333120617 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡

የደሴ ከተማ አስ/ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Dessie City Urban & Infrastructure Development Department seeks suppliers for office supplies, cleaning materials, fixed assets, building tools, vehicle spare parts, garage maintenance services, tires and batteries, across 11 lots under an annual contract. Bidders need a renewed sector trade license, TIN, and competency certificate; VAT registration required if purchase exceeds 500,000 birr.
Save Tender