የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ዋናው መ/ቤት) ለውሃ ቁፋሮ ስራ አገልግሎት የሚውል የዕቃ አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 01/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Water Works Construction Enterprise (WWCE) (የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን)
ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB WWC 01/2019
የውኃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ዋናው መ/ቤት) ለውሃ ቁፋሮ ስራ አገልግሎት የሚውል የዕቃ አቅርቦት ህጋዊ ከሆኑ ድርጅቶች በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ በጨረታ ቁጥር NCB WWC 01/2019 አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ አቅራቢዎች የሚከተሉትን ህጋዊ ሁኔታዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
| ተ.ቁ | የሎት | ዋና ዋና የዕቃ ዝርዝር/ዓይነት Summery of goods | መለኪያ | ብዛት | ምርመራ |
| 1 | ሎት-1 | Difference types of Steel Casing | በቁጥር | 625 | |
| 2 | ሎት-2 | PH/EC/TDS/Temperature portable meters (Por-table water Quality kit) | Set | 5 |
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
1. የዘመኑን ግብር ከፍለው በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፤የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/TIN/፤የቫት ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው መሆን አለበት፡፡ ተጫራቾች እነዚህንና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን መረጃዎች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በመጫረቻ ሰነዶቻቸው ላይ ማካተት ይጠበቅባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚሆን ለ60 ቀን እና ከዚያ በላይ ጸንቶ የሚቆይተጨማሪ እሴት ታከስን ጨምሮ ለሎት-1 ብር 400,000.00 /አራት መቶ ሺህ ብር/፣ለሎት-2 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር/ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /ሲ.ፒ. ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በማሰራት ማስያዝ አለባቸው፡፡
3. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 /ሃያ/ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በመምጣት የማይመለስ ብር 1,000 /አንድ ሺህ ብር/ በውሀ ስራዎች ኮርፖሬሽን ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው ከኮርፖሬሽኑ ዋና ግቢ ከጠቅላላ ሒሳብ ከፍል ቢሮ እና አዲስ አበባ ከሚገኘው ከአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሳሪስ ቦንጋ ሆቴል ገባ ብሎ 100 ሜትር በመሄድ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች መወዳደሪያ ሀሳባቸውን ማለትም የቴከኒከና የዋጋ ሰነዳቸውን በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ቴከኒካልና ፋይናንሻል በተናጠል/ለየብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ባህር ዳር ከተማ ከሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
5. የቴክኒካል ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከኮርፖሬሽኑ ዋናው መ/ቤት ግቢ ግዥና አቅርቦት ዳይሬከትሬት ቢሮ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ተዘግቶ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
7. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ቢሮ ግዥ እና አቅርቦት ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቁጥር 25 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም ስልክ ቀጥር- 058222-14-79 መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
8. ማሳሰቢያ፤- አዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የጨረታ ሰነድ መግዛት ብቻ እንጂ የጨረታ ፖስታውን ማስገባት የሚቻለው ባህርዳር ዋናው መስሪያ ቤት መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
አድራሻ: - ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 14 የድሮው አዲናስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ፖ.ሣ.ቁ 106, ስልክ ቁጥር 0582221479
የውሃ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋናው መ/ቤት
