አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከላይ በሎት የተጠቀሱትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ
በድጋሚ የወጣ የሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር:-AAU/NCB/pdi/10/2019/26
ያገለገሉ ቁርጥራጭ ብረቶች ሽያጭ ጨረታ
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከላይ በሎት የተጠቀሱትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- እቃዎቹ የሚገኙበት አድራሻ 6 ኪሎ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ንብረት አስተዳደር ክፍል ሲሆን ለመግዛት ፍላጎትና ብቃት ያላቸው ተጫራቾች በታሸገ ኢንቨሎፕ የጨረታ ሰነድ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንድታቀርቡ ተጋብዛችኋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያ ሥነ-ሥርዓት መሰረት ይፈፀማል፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ሀ) በተገለፀው አድራሻ የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000087392067 ገቢ በማድረግና ደረሰኙን ይዘዉ በመቅረብ ስለእቃዎቹ ሙሉ ዝርዝር የያዘዉን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ዘግይተዉ የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸዉም፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቁጥር 7 (ሐ) በተጠቀሰዉ አድራሻ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 7 (ለ) በተገለጸዉ አድራሻ ጥቅምት 20 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ወይም በፊት በግዥ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ከጨረታ መዝጊያ ጊዜ በፊት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ ተጋባዥ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በዩኒቨርሲቲው ስም አሰርተዉ አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸው፡፡ በተጨማሪም ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች ከዉድድሩ ከወጣ የተያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ የሚወረስ ይሆናል፡፡
- ሀ/ ሰነዶቹ የሚሸጡበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ግዥ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 307
ለ/ የጨረታዉ ሰነድ የሚገባበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200
ሐ/ ጨረታው የሚከፈትበት አድራሻ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 200 - የጨረታ አሸናፊዉ ድርጅት ወይም ግለሰብ የዉል ስምምነት ከተፈረመበት ቀን በኋላ ባሉት 10 ቀናት ውስጥ ለዩኒቨርሲቲው ሙሉ ክፍያ በመፈጸም ከከፈለበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን እቃ ማንሳት አለበት፡፡
- ዩኒቨርሲቲዉ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታዉን የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ስልክ ቁጥር 011-122-00 01/011-124-32-72 ፖ.ሣ.ቁ 1176
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ
✨ messages.ai_summary
Addis Ababa University invites eligible bidders to buy used scrap metals via open bid; items are located at its 6 Kilo Property Administration office. Bidders must submit sealed documents and a bid security in the university's name. The university may cancel the tender in part or fully.
