በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለህክምና አገልግሎት የሚውል Rack Tower Server ግዥ በግልፅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በማሳወጅ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2019 በጀት ዓመት ለህክምና አገልግሎት የሚውል Rack Tower Server ግዥ በግልፅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በማሳወጅ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ አግባብና ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኦርጅናል እና ኮፒ
- የመንግስት ግዥ በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ኮፒ
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ከፍያ የምስክር ወረቀት /TN Number/ ኦርጅናል እና ኮፒ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ኦርጅናል እና ኮፒ በተለያዩ ፖስታ ካሸጉ በኋላ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
እያንዳቸው ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ብቻ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ /RV/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማኖር ዋናውን ሰነድ በአግባቡ በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በግልፅ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን /VAT/ የሚያካትት መሆን አለበት፡፡
የጨረታው ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር ብቻ/ ሆስፒታላችን ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብና በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላል፡፡
የጨረታው ዶክመንት በታሸገ ኤንቨሎፕ አድራሽ በመፃፍ ሕጋዊ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች፡-
ከላይ የተገለፀውን በ16ኛው የሥራ ቀን በሆስፒታላችን ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ፖስታ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ ሲሆን የጨረታው መከፈቻ ቀን ቅዳሜ ዕሁድና የበዓላት ቀን ላይ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
በ16ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ላይ የታሸገው የጨረታ ሳጥን ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች በጨረታ መከፈቻ ሰዓት ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡ ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0937054906 / 0912750304 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
የአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል
