የጽፈት መሳሪያ፣ የመኪና ጎማ፣ ፈርኒቸር፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የደንብ ልብስ፣ የቴክኒክ እና ሙያ እቃዎች ግዢ እና የፒካፕ መኪና እና ትንንሽ የቤት መኪና ኪራይ
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ከ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት ለመጀመሪያ ዙር ለሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሚውሉ
A. የጽፈት መሳሪያ B. የመኪና ጎማ C. ፈርኒቸር D. ኤሌክትሮኒክስ E. የደንብ ልብስ G. የቴክኒክ እና ሙያ እቃዎች ግዢ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ እና H. የፒካፕ መኪና እና ትንንሽ የቤት መኪና ኪራይ መከራየት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጸውን መመሪያ መረጃዎች በማቅረብ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
- በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- አቅራቢዎች ዝርዝር ተርታ የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን/ ተመዝጋቢ የሆኑ፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት እና በሥራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 1500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ) ብር በሲንቄ ባንክ አካውንት 1064934721214 በማስገባት (በመክፈል) በገላን ከ/ከተማ ገቢዎች ባለሥልጣን ጽ/ቤት ወደ ደረሰኝ በመቀየር ሰነዱን ከገላን ከ/ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር (ሰነድ) ዋና እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ/ በፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ በገላን ከ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ባዘጋጀነው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የመኪናውን ሙሉ መረጃ (ሊብሬውን) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥን ታሽጎ (ተዘግቶ) ልክ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በገላን ከ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የማይገኙ ከሆነ ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን አሸናፊነቱ ከተገለጸላቸው በኋላ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በማስያዝ ውል መዋዋል ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን አሸናፊነት ከተገለጸላቸው በኋላ ውል ካልፈጸሙና የውል ማስከበሪያ ካላስያዙ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ውስጥ በተገለጸው መሠረት የተጫረቱበትን የእቃ ናሙና /Sample/ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ውስጥ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለው ማለት አይችልም፡፡
- የመወዳደሪያ ዋጋ በጨረታ ሰነዱ በተዘረዘረው መሠረት ተሞልቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 4 45 01 82 ወይም 0923574941 በመደወል እና በአካል ተገኝቶ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
አድራሻ፡- በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ከ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በሸገር ከተማ አስተዳደር የገላን ክ/ከተማ ገ/ጽ/ቤት
✨ messages.ai_summary
- Procurement of stationery, vehicle tires, furniture, electronics, uniforms, technical and vocational items, and rental of pickup trucks and small cars.
- Issued by the Gelan Sub-city Administration Office, Sheger City, Oromia Regional Government.
- Bid document price: ETB 1,500 (non-refundable). Bid bond: ETB 100,000 via bank-confirmed CPO only.
- Tender box closes on the 16th day at 4:00 PM and opens the same day at 4:30 PM.
- Eligibility includes a valid renewed license, paid current taxes, VAT and TIN registration, tax clearance; vehicle rental bidders must provide full vehicle logbook, and samples must be submitted as specified.
