Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline04 Sep 2026, 2:30 PM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityከ1/4ኛው
  • opening date2026-09-04 14:30:00
  • Categories Land , House, Building And Warehouse , Land, House, Building And Warehouse Rent

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

 

በፍ/ባለመበት ወ/ሮ ይምጡ በዝና ጋሻው እና በፍባለዕዳ አቶ ታደለ ደባይ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 228431 030/12/2014 እና 289408 በ14/2/2015 ዓ.ም በመ/ቁ.289408 በቀን 21/05/2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በአራዳ ኪ/ከተማ ወረዳ 4 የቤቱ 523 የሆነው በካርታ ቁጥር ኮ/9/12/260/75 የቦታ ስፋት 172 ኪ.ሜ የሆነ ቤት ይዞታው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጥናት 2 ሜትር ይነካዋል የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,828,964 ( እንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሃያ ስምንት ሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ አራት) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 28 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቶች ምዝገባ በ8፡30 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ C.P.O ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ ጨረታው በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም C.PO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ስበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ

የምትችሱ መሆኑን እንገልጻስን፡፡

 

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

Save Tender