አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
Amhara Bank S.C (አማራ ባንክ አ.ማ)
የሐራጅ ማስታወቂያ
ቁጥር አማራ ባንክ 56/2019
አማራ ባንክ አ.ማ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 216/92 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ከዚህ ቀጥሎ የቀረበውን ንብረት በግልጽ የሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
| ተ.ቁ | የተበዳሪው ስም | የንብረት አስያዥ ስም | አበዳሪው ቅርንጫፍ | የንብረቱ አድራሻ ክ/ከተማ | ከተማ | ወረዳ | ቀበሌ | የቦታው ስፋት | የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ ቁጥር | የንብረቱ ዓይነት/ የይዞታው አገልግሎት | የጨረታ መነሻ ዋጋ /ብር/ | ጨረታው የሚካሄድበት ቀን | ሰዓት | ቦታ |
| 1 | አስናቀ እጅጉ አንተነህ | ወ/ሪት ቤዛዊት እጅጉ አንተነህ | ሳር ቤት | ኮ/ ቀራንዮ | አዲስ አበባ | 4 | - | 150 ካ.ሜ | K05/02-3-130-183-8260/01 | ለመኖሪያ | 8,128,007.98 | ኅዳር 18 ቀን 2019 ዓ.ም | ከ 4:00 እስከ 5:00 ሰዓት | አማራ ባንክ አ.ማ ዋናው መስርያ ቤት |
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ ¼ ወይም ሃያ አምስት በመቶ (25%) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (C.P.O) ብቻ በአማራ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት; በማስያዝ እና በመመዝገብ በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ::
- ከፍተኛ ዋጋ የሰጠው ተጫራች የጨረታው አሸናፊ ነው የሚባለው ከባንኩ አሸናፊነቱን የሚገልጽ ደብዳቤ በጽሁፍ ሲደርሰው ብቻ ነው::
- የጨረታ አሸናፊው አሸናፊ መሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ቀናት ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠናቆ መክፈል ይኖርበታል:: ባይከፍል ግን የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ያስያዘው ሲፒኦ አይመለስለትም፤ ለባንኩ ገቢ ይሆናል:: በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሃራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል:: ላላሸነፉት ተጫራቾች ግን ያስያዙት ሲፒኦ በእለቱ ይመለስላቸዋል::
- የሐራጁ አሸናፊ /ገዥ/ ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን የሊዝን ክፍያን ጨምሮ፤ ግብር፤ በዋጋው ላይ ሚታሰብ ተጨማሪ እሴት ታክስ (15%) ካለ ከስም ማዛዋወሪያ ጋር የተገናኙ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰኑ ታክስ እና ግብሮች ገዥው/አሸናፊው/ ይከፍላል::
- ተጫራቾች በሃራጅ ለመሳተፍ ሲመጡ መታወቂያ (የቀበሌ፤ የመንጃ ፍቃድ፤ ፓስፖርት ወይም ብሄራዊ መታወቂያ) መያዝ ይገባቸዋል:: ተጫራቾች የህግ ሰውነት የተሰጣቸው አካላት ከሆኑ ደግሞ ህጋዊ ሰውነት ያገኙበትን የዋና ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሃራጁን ለመሳተፍ የቀረበው ግለሰብ ስልጣኑን የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የጸደቀ መመስረቻ ጽሁፍ(የመተዳደሪያ ደንብ)፤ ቃለጉባኤ ወይም የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት::
- ንብረቱ በገገርው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል::
- ለሐራጅ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጉብኝት ፕሮግራም ከወርካዉትና ሪከቨሪ ክፍል ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ ጨረታው ከመካሄዱ ከ5 ቀን በፊት መጎብኘት ይችላል::
- ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን፤ ሰዓትና ቦታ ተጫራቾች፤ ተበዳሪ እና ንብረት አስያዥ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል:: ነገር ግን ተበዳሪውም ሆነ መያዥ ሰጪዉ ባይገኙ ጨረታው በሌሉበት ይካሄዳል::
- ንብረቱን/ቶቹን በጨረታ አሸንፎ የገዛ ግለሰብ/ድርጅት የሽያጭ ገንዘቡን ከፍሎ ባጠናቀቀ በ15 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን መረከብ ያለበት ሲሆን በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ካልተረከበ በንብረቱ ላይ ለሚደርስ ጉዳት ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም:: ገዥው በተጠቀሰው ጊዜ ንብረቶቹን ካልተረከበ ከንብረቶቹ ጋር በተያያዘ ለሚኖር ወጪ ኃላፊነቱን ይወስዳል::
- በባንኩ የብድር ፖሊሲ፣ መመሪያ እና ቅድመ ሁኔታ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ለተጫራቹ እስከ 100% ብድር ሊያመቻች ይችላል ::
- የተጫራቾች ምዝገባ ከሃራጁ መዝጊያ ሰአት 30 ደቂቃ በፊት ይጠናቀቃል::
- በወንድ አንቀጽ የተጠቀሰው ለሴት እና ህጋዊ ሰውነት ላላቸው ድርጅትም ያገለግላል::
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
- ለበለጠ ማብራሪያ አማራ ባንክ አ.ማ 0115 58 27 64 ወይም 011 5 58 41 89 በስራ ሰአት ደውለው መጠየቅ ይችላሉ::
አማራ ባንክ አ.ማ.
✨ messages.ai_summary
Amhara Bank is selling a residential property in K/Keraniyo, Addis Ababa (Sar Bet branch), via open auction. Bidders must present ID or legal-entity documents and a 25% CPO in the bank's name. The highest bidder wins upon written notice and must pay the balance within 15 days.
