የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት አመት ለሴከተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ ሞተር ሰይከልሎችን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
የጨረታ ማስታወቂያ
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለ2018 በጀት አመት ለሴከተር መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሰጡ ሞተር ሰይከልሎችን በዘርፉ የተሰማሩ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ።
በመሆኑም:-
♦️ የዘመኑን የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ
♦️የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል
♦️ የአቅራቢነት ምዝገባ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችል
♦️የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
♦️የጨረታ ማስከበሪያ ብር 70,000 (ሰባ ሺ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
♦️ ተጫራቾች ሰነዱን ከስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ) ብር ብቻ በመከፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ፋይናንሻል አንድ ኦርጂናል እና 2 ኮፒ ለየብቻ እንዲሁም ቴከኒካል ዶክመንቱን አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ሳጥኑ በoኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 10ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ
ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡ መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
ሰበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0467710586
የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
