Tender Detail

Tender Details


በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ በዚህ በ2018 በጀት ዓመት የእንስሳት መድኃኒት የእንስሳት መኖ፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ የመኪና ጥገና ጋራዥ አገልግሎት ግዥ በአገር ውስጥ ገበያ በገልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ሠመራ


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ በዚህ በ2018 በጀት ዓመት የእንስሳት መድኃኒት የእንስሳት መኖ፣ የመኪና መለዋወጫ ዕቃ፣ የመኪና ጥገና ጋራዥ አገልግሎት ግዥ በአገር ውስጥ ገበያ በገልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፁትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

1)     ተጫራቾች ግዴታ ማሟላት ያለባቸው የቅደሚያ መወዳደሪያ መስፈርቶች ማለትም፡-

1.     በዘርፉ የዘመኑ የታደሠ ንግድ ፈቃድ

1.2  የንግድ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው

1.3  ንግድ ፈቃድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያለው

1.4  የተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ የሆነ

1.5  ሲ.ፒ.ኦ

1.6  የጨረታ ሰነድ ግዥ የፈጸመ እና

1.7  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2)     በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ በግዥ /ፋይ/ ንብ/አስ/ ደጋፊ ዳይሬክተር የስራ ሂደት ክፍል ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

3)     ተጫራቾች በእያንዳንዱ በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነዶች ላይ ተጫራቾች ወይም የህጋዊ ወኪል ፊርማና ማህተም ማኖር ይኖርባቸዋል፡፡

4)     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና / Bank Guarantee / ለውድድር የሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 1% በሲ.ፒ.ኦ (C.P.O) የጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

5)     የጨረታ ተወዳዳሪዎች በውድድሩ ከተሸነፉ ለዋስትና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናና እንዲሁም ናሙና የጨረታው ውጤት ታውቆ ውል ከተፈራረሙ በኋላ ወዲያውኑ የውል ማስከበሪያው ይመለስላቸዋል።

6)     ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርቡትን የውድድር ጥያቄ መ/ቤቱ አይቀበልም፡፡

7)     ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በእለቱ 4፡30 ሰዓት በአፋር ብሄራዊ ከልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8)     ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

9)     ለተጨማሪ መረጃ በቢሮው ስልክ ቁጥር 09-12-97-77-98 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

 

በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ

ሠመራ

 

Save Tender