የፈሳሽ ናይትሮጅን ማምረቻ ማሽን (2) ግዥ (እ/አ/ሀ/ል/ቢ/ግጨ/01/05/19) - የአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ
የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ቢሮ
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-እ/አ/ሀ/ል/ቢ/ግጨ/01/05/19
በአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ለእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ አገልግሎት የሚውል የፈሳሽ ናይትሮጅን ማምረቻ ማሽን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፤ ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርት የምታሟሉ ሁሉ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር {TIN} ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን 500,000/ አምስት መቶ ሺህ/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ {VAT} ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዛው የፈሳሽ ናይትሮጅን ማምረቻ ማሽን ብዛት 2/ሁለት/ ሲሆን የዕቃዎችን ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፍኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 2,000,000/ ሁለት ሚሊዮን ብር / በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ መይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ከቴክኒካል ዶክመንቱ ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሁለት የተለያየ ኢንቨሎፕ ቴክኒካል የመወዳደሪያ ሀሳብ እና ፋይናንሻል የመወዳደሪያ ሀሳብ በማለት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ የኢትዮጵያ 300.00( ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ጨረታ ሰነድ የወሰዱ ተወዳዳሪዎች የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከ18/02/2019 ዓ.ም እስከ 07/03/2019 ዓ.ም በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ08/03/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 0583207434 በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- አድራሻ፡- ባህር ዳር ቀበሌ 3 አብክመ ግብርና ቢሮ ጎን
የአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ቢሮ /ባህር ዳር/
✨ messages.ai_summary
The Amhara Bureau of Livestock and Fisheries seeks to buy two liquid nitrogen production machines for animal breed improvement. Bidders must hold a valid trade license, TIN, and VAT registration certificate if the purchase exceeds 500,000 birr, submitting copies with their bid.
