የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢ መለያ ቁጥር፡-ሲ/መ/ባ/001/2018
የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን በተለያዩ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ጠጠር የሚያመላልሱ ገልባጭ መኪኖች እስከነ ሎደሩ አቅራቢዎችን ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የፕሮጀክቱ ስም |
በክልል ውስጥ መንገዱ የሚገኝበት ወረዳ |
የመንገዱ ርዝመት በኪ/ሜ |
|
1 |
ሽልቾ አበራ ሁላ |
ዳራ ኦትልቾ |
10 |
|
2 |
ዳምሌ ጭራቻ ባዳሎ |
ቦና |
10 |
|
3 |
ሀገረ ሰላም ጋታማ |
ሁላ |
13.3 |
በዚሁ መሠረት፡-
1. የኮንስትራከሽን መሣሪያዎች የማከራየት ፍቃድ ያላቸው ሆነው በመንገድ ሥራ ላይ፣
2. ገልባጭ መኪና እስከነ ሎደር የስሪት ዘመን እ.አ.አ 2012 እና ከዚያ በላይ ሆኖ፣ የተሽከርካሪ የመጫን አቅም=14m3 የሆነ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት እና በጨረታ መወዳደርየሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሰርተፊኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. አዲስ ስራ ፊቃድ የሚያቀርቡ ተጫራቾች ከአንድ ፕሮጀክት በላይ እና እንዲሁም ሥራ ልምድ ያላቸው ተጫራቾች ደግሞ ከሁለት ፕሮጀክቶች በላይ መወዳደር አይችሉም፡፡
5. ከሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን ጋር ውለታ ገብቶ በአፈጻጸም ችግር ምከንያት ማስጠንቅቄያ ተሰጥቶ ስራውን ያላጠናቀቄና ውሉ የተቋረጠ የገልባጭ መኪና አከራይ ድርጅት የጨረታ ሰነዱን መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችልም፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አሰራ) ተከታታይ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት ግዥ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከቶሬት ቢሮቁ ጥር -5 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ የ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ዋስትና (Unconditional Bid Bond) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በተገለጸው መሠረት ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ180 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል፡፡
8. የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመርያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማሰከበርያ /Bid Security/ ፋይናሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንድሁም ቴከንካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒ ሰነዶች በተለያየ ፖስታ በሰም በማሸግ ለየብቻቸዉ ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታው ተካተውና በሁሉም ዶከመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማዕተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይረክቶሬት ክፍል ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሠነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት። ሆኖም የተጠቀሰው ቀን የእረፍት ወይም የህዝብ በዓል ቀን ሆኖ ከዋለ በቀጣይ በስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በባለስልጣኑ መ/ቤት አደራሽ ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0462-128-446
ሲዳማ መንገዶች ባለሥልጣን (ሀዋሳ)
