የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችንና አገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል።
ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 003/2018 በጀት ዓመት
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት ጥራቱን የጠበቀ ግዥ ለመፈጸም ስለፈለግን
የተሽከርካሪ እቃና ጎማዎች፤ እስቴሽነሪ፤ የጽዳት እቃ፤ የደንብ ልብስ፤ የደንብ ልብስ ስፌት፤ ከ24ሰው በላይ የሚጭን የህዝብ ትራንስፖርት፤ የጭነት መኪና ከ50ኩንታል በላ የሚጭን፤ ፒካፕ የጭነት መኪና፤ ህትመት
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን እቃዎችንና አገልግሎት ግዥዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት እና ለማሰራት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት ቀጥሎ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢ ተጫራቾች በጨረታው እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የአገልግሎት ግዥ እና የሚያስገቡት እቃ ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።
- ለወጣው ጨረታ በዘርፍ የተሰማሩ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የቲንነበር ተመዝጋቢ የሆኑና የንግድፍቃዱና ቲንነበሩ ተናባቢ የሆነ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ማሟላት የሚጠበቅባቸው የቫት የገቢዎችን መመሪያ የሚያሟላ መሆን አለበት) ተመዝጋቢ የሆኑ ሠነዱን ሲያስገቡ ኦርጅናልና ኮፒው በማህተም የተደገፈና የባለቤትነት ሁኔታ ግልጽ የሚያደርግ ሌላ ህጋዊ ተጨማሪ ማስረጃ ካለ በማያያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በብር መጠን በየሎቱ እደሚከተለው በየሎቱ ማስያዝ አለባቸው።
- ሎት1. እስቴሽነሪ 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት2. የጽዳት እቃዎች 10 ,000 ብር (አስር ሺህ ብር)
- ሎት3. የደንብ ልብሶች እና ስፌት 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት4. የመኪና እቃዎች 10,000 ብር (አስር ሺህ ብር)
- ሎት5. የህዝብ እና የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት 5,000 ብር (አምስት ሺህ ብር)
- ሎት6. ህትመት 2,000 ብር (ሁለት ሺህ ብር)
በማስያዝ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ በመግዛት ዋጋውን ሞልቶ ማስገባት አለበት በአስረኛው ቀን 11፡30 ላይ ታሸጎ ጨረታው በተጠናቀቀ ማግስት ወይም በአስራ አንደኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ሁሉም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የእቃና የአገልግሎት ግዥ እንደማይሳተፋና ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እንደሚወረስ ማወቅ ይኖርባቸዋል።
- ለጨረታው ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ጽ/ቤቱ 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት ወረዳ12 ፋይናንስ ጽ/ ቤት እቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ ያልተሟላ ከሆነ ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ መገንዘብ ይኖርባቸዋል። ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።ነገርግን ጽ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ጨረታውን በተናጠልም ሊሰርዝ ይችላል።
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ ግልጽ ያልሆነ ነገር ካለ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት ከአዲሱ ህንፃ 6ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርቦ መግዛት ይችላሉ። ሰነድም ሲያስገቡ በዚሁበ 6ኛ ፎቅ ላይ ነው። ነገር ግን ሰነድ በነጻ የሚወስዱ ተጫራቾች የሚያጽፉት ደብዳቤ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ላይ እሴት የሚጨምሩበት መሆኑን ተገልፆ መጻፍ አለበት።
- ማንኛውም ሰነድ ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በቀረበው የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ማድረግም ይሁን ማሻሻያ ማቅረብ ወይም ከጨረታው እራሱን ማግለል አይችልም፣ይህ ሆኖ ከተገኘ በጨረታው ህግ መሰረት የሚቀጣ መሆኑን መገንዘብ ይኖርበታል።
- ጨረታውን ሲያስገቡ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር: 09-21 698 915/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ የወረዳ 12 ፋይናንስ ጽ/ቤት ታክሲ ማዞሪያው ፖሊስ ጣቢያው ጋር እንገኛለን።
የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
