የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከዩኒሴፍ፣ GEQIP-E PfoB እንዲሁም ከመንግስት በተገኘ በጀት ለቢሮ አገልግሎት፣ ለተማሪዎች መማሪያ አገልግሎት ለስደተኛ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አገልግሎት የሚውሉ የትምህርትና የንጽህና ቁሳቁሶች፣ ለጥጉ ሠራተኞች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ እንዲሁም ለቢሮው አይሲቲ፣ ለስደተኛ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ እና ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ሰርተፍኬት ህትመት የሀገር በቀል ሶፍትዌርን በመጠቀም ለመመዝገብና ፈተናውን ለማረም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ከዚህ በታች ከ1 እስከ 4 ሎት የተዘረዘሩትን የተለያዩ ቁሳቁሶችን በስራ ዝርዝራቸው ወይም ስፔስፍኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018
የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከዩኒሴፍ፣ GEQIP-E PfoB እንዲሁም ከመንግስት በተገኘ በጀት ለቢሮ አገልግሎት፣ ለተማሪዎች መማሪያ አገልግሎት ለስደተኛ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አገልግሎት የሚውሉ የትምህርትና የንጽህና ቁሳቁሶች፣ ለጥጉ ሠራተኞች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ እንዲሁም ለቢሮው አይሲቲ፣ ለስደተኛ ትምህርት ቤቶች ድጋፍ እና ለ6ኛ እና ለ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናን ከምዝገባ ጀምሮ እስከ ሰርተፍኬት ህትመት የሀገር በቀል ሶፍትዌርን በመጠቀም ለመመዝገብና ፈተናውን ለማረም አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ከዚህ በታች ከ1 እስከ 4 ሎት የተዘረዘሩትን የተለያዩ ቁሳቁሶችን በስራ ዝርዝራቸው ወይም ስፔስፍኬሽን መሠረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
እነሱም፡-
- ሎት (1) የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ግዥ፣
- ሎት (2) የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ
- ሎት (3) የሠራተኞች ደንብ ልብስ ግዥ እና
- ሎት (4) የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ናቸው።
ስለዚህ የሚከተሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በዘርፉ መወዳዳር የሚችሉ መሆኑ ይጋብዛል።
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በአቅራቢነት የተመዘገቡበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ የማስረጃዎቹን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የዕቃዎቹን ዝርዝር መግለጫ ስፔስፍኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር 2% /ሁለት ፐርሰንት/ ብቻ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ CPO /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /ቢዲ ቦንድ/ ወይም ጥሬ ገንዘብ ከዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን በግልጽ የመወዳደሪያ ሠነዶቻቸውን ኦርጅናሉንና ፎቶ ኮፒውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ተከታታይ ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 08 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ቀኑ ቅዳሜ /እሁድ/ ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው ቀን ይከፈታል።
- አሸናፊ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን 10% በማስያዝ ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸው በ7 ቀናት ውስጥ ውል ባይገቡ ለጨረታ ያስያዙት 2% ለመንግስት ገቢ ይደረጋል።
- ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡበት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፋቸውን ቁሳቁሶች ቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ መጋዘን ድረስ በራሱ ትራንስፖርት ማስረከብ አለበት።
- ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት ላይ ባይገኙ የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።
ለበለጠ መረጃ፡- ቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ የግዥ/ ንብ/አስ/ር ዳይሬክቶሬትን በስልክ ቁጥር 0577752979 መጠየቅ ይችላሉ።
የቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል መንግስት ት/ቢሮ
