Tender Detail

Tender Details


ለደቡብ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሸካ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች/ የጽሕፈት መሣሪያዎች/፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የፋይል መክፈቻ (የሕትመት ሥራዎች)፣ ላፕቶፕ ኮር አይ7 (Hp Lap Top Core i7) ላፕቶፕ ኮር አይ5(Hp Lap Top Core i5) ላፕቶፕ ኮር አይ3 (Hp Lap Top Core i3)፣ የኃላፊ ቢሮ ወንበርና ጠረጴዛ፣ የችሎት አዳራሽ ወንበር የእንግዳ መቀመጫ፣ የችሎት አዳራሽ ወንበር ዕድሳትና ጥገና፣ የጋራ አገልግሎት የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ለቢሮ መስኮትና ለጠረጴዛ የባህል ልብስ መጋረጃ፣ ኮምፒውተር፣ ኮፒ ማሸን፣ RTR 180CC ሞተር ሳይክል፣ TVS 150CC ሞተር ሳይክል፣ TVS 125CC ሞተር ሳይክል፣ RTR 180CC ሞተር ሳይክል ጎማ፣ TVS 125CC ሞተር ሳይክል ጎማ፣ RTR 180CC ሞተር ሳይክል ዕድሳትና ጥገና፣ TVS 125CC ሞተር ሳይክል ዕድሳትና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ በቤንች ሸኮ ዞን የሸካ ወረዳ ፍርድ ቤት


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ለደቡብ/ም/ኢ/ህ/ክ/መ/የቤንች ሸኮ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሸካ ወረዳ ፍርድ ቤት ለ2018 በጀት ዓመት ለመ/ቤቱ አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ የቢሮ አላቂ ዕቃዎች /የጽሕፈት መሣሪያዎች/፣ የጽዳት ዕቃዎች፣ የፋይል መክፈቻ (የሕትመት ሥራዎች)፣ ላፕቶፕ ኮር አይ7 (Hp Lap Top Core i7) ላፕቶፕ ኮር አይ5(Hp Lap Top Core i5) ላፕቶፕ ኮር አይ3 (Hp Lap Top Core i3)፣ የኃላፊ ቢሮ ወንበርና ጠረጴዛ፣ የችሎት አዳራሽ ወንበር የእንግዳ መቀመጫ፣ የችሎት አዳራሽ ወንበር ዕድሳትና ጥገና፣ የጋራ አገልግሎት የሠራተኞች የደንብ ልብስ፣ ለቢሮ መስኮትና ለጠረጴዛ የባህል ልብስ መጋረጃ፣ ኮምፒውተር፣ ኮፒ ማሸን፣ RTR 180CC ሞተር ሳይክል፣ TVS 150CC ሞተር ሳይክል፣ TVS 125CC ሞተር ሳይክል፣ RTR 180CC ሞተር ሳይክል ጎማ፣ TVS 125CC ሞተር ሳይክል ጎማ፣ RTR 180CC ሞተር ሳይክል ዕድሳትና ጥገና፣ TVS 125CC ሞተር ሳይክል ዕድሳትና ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሰረት-

  1. በዘርፋ የተሰማሩበትን የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፌኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. በዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ ያየዘ ሰነድ /Specification/ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ እስከ 21 (ሃያ አንድ) ተከታታይ የሥራ ቀን ዘወትር በሥራ ሰዓት በሸኮ ወረዳ ፍርድ ቤት የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ር/ደ/ሥራ ሂደት በቢሮ ቁጥር 06 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቶች ዋጋቸውን ሞልተው የሚያቀርቡት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተቀመጠው የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎት የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ በሚለው የዕቃዎች ዝርዝር መሠረት ብቻ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን በወሰዱት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም አርፎበትና ተፈርሞበት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ የዕቃ ዋጋ 2% በባንክ በተመሰከረ ቼክ /C.P.O/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  9. የጨረታው ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የሥራ ቀን ክፍት ሆኖ ከቆየ በኋላ በ22ተኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በተመሳሳይ ቀን ከጠዋት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  10. የጨረታ መክፈቻ ቀን የበዓል ቀን ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡
  11. የተጫራቾች ተሟልቶ አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሥነ-ሥራዓቱን አያስተጓጉልም፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- +251477780226/+251929943390/ +251908402189

 

የደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መ/ በቤንች ሸኮ ዞን የሸካ ወረዳ ፍርድ ቤት

 

Save Tender