በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 001/2018
በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን ዕቃዎች በሎቱ መሰረት፡-
|
ሎት |
የዕቃው አይነት |
የብር መጠን |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 8,000 |
|
ሎት 2 |
አላቂ የማስተማሪያ እና የፅህፈት መሳሪያዎች |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 10,000 |
|
ሎት 3 |
አላቂ የፅዳት እቃዎች |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 14,000 |
|
ሎት 4 |
የጥገና እቃዎች እና የስራ እቃዎች |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 3,000 |
|
ሎት 5 |
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችና (ኮምፒውተር እቃዎች) |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 41,000 |
|
ሎት 6 |
ፎቶ ኮፒ ማሽን ጥገና |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 2,000 |
|
ሎት 7 |
ቋሚ እቃዎች |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 12,000 |
|
ሎት 8 |
የተለያዩ ህትመት ስራዎች |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 2,000 |
|
ሎት 8 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን 2,000 |
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩትን ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል በዚህም መሰረት፡
- በጨርታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን፤ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና በመንግስት ግ/ን/አስተዳደር ኤጀንሲ ደህረ ገፅ ላይ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨርታውን ሰነድ በማይመለስ 100 ብር በመክፈል ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ ት/ቤቱ ፋይናንስና ገዥ ንብረት አስተዳደር ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ሰዓት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በት/ቤቱ ፋይናንስ ግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ለጨርታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደርባቸውን እታዎች ለእያንዳዳቸው ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 10ኛው ቀን 11:30 ታሽጎ በማግስቱ ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥልው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፤ ሎት 2፤ ሎት 3፤ ሎት 4፤ ሎት 6፤ ሎት 8፤ ሎት 9 ላይ ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 5 እና ለሎት 7 በቀረቡ የፍላጎት መግለጫ መሰረት የተሟላ የፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ገዥው ፈፃሚ መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዥ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ እና ጥያቄ፤ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ዳርማር ጫማ ፋብሪካ አጠገብ ወይም ከልደታ ፍርድ ቤት ጀርባ ደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት 0118685799 ወይም 0118964301 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በልደታ ክፍለ ከተማ የደጃ/ባልቻ አባነፍሶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
