የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለ2018 በጀት አመት ለማእከሉ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የህንጻ መሳሪያዎች ፤ የሀክምና እቃዎች፣ የመብራት መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ የመኪና ዘይት እና ቅባት፣ የፎቶ ኮፒና የኮምፒውተር ጥገና አገልግሎት አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ መስ/ዞን ደሴ አካል ተሀድሶ ማዕከል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ አካል ተሀድሶ ማእከል ለ2018 በጀት አመት ለማእከሉ አገልግሎት የሚውሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች ፣ የህንጻ መሳሪያዎች ፤ የሀክምና እቃዎች፣ የመብራት መለዋወጫ ዕቃዎች፣ የህትመት ስራዎች፣ የመኪና ዘይት እና ቅባት፣ የፎቶ ኮፒና የኮምፒውተር ጥገና አገልግሎት አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም፡-
- የታደስ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የግብር መክፈያ ቁጥር /TIN/ ያለው የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ፣ ህጋዊ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትን የሚያሟላ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች የጨረታ መመሪያውንና የእያንዳንዱን እቃዎች ዝርዝር መግለጫ / Specification / የያዘ የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ሰነዱን ቢሮ ቁጥር 7 መግዛት ይቻላል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ በሞሉት ጠቅላላ ዋጋ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ 1% / አንድ ፐርሰንት/ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
- የጨረታ ውድድሩ የሚደረገው በሎት ሆኖ በጠቅላላ ዋጋው ነው።
- ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ የተጋነነ ዋጋዎችን በገበያ ጥናት መሰረት በማድረግ ከውድድር ውጭ የምናደርግ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የጨረታ ሰነዱ በታሸገ ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ከ15ኛው ቀን ቀጥሎ በዋለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ድረስ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 7 በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ሳጥን ማስገባት ይጠበቃል።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ቀጥሎ በሚውለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በእለቱ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በማእከሉ ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሁሉም ተጫራቾች በአካል ባይገኙም በእለቱ የጨረታ ሰነዱ ተከፍቶ ከታየ በኋላ ተገቢው የጨረታ ማስከበሪያ መኖሩ ከተረጋገጠ ተጫራቹ በአካል ባይገኝም ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታ አሸናፊው በተሰጠው የጨረታ ሰነድ /Specification/ መሰረት ለማቅረብ ውለታ በወሰደበት ቀናት ውስጥ በራሱ ትራንስፖርት አጎጉዞ በማቅረብ በሚመለከታቸው ቴክኒክ ባለሙያ እየተረጋገጠ ለማእከሉ ን/ክፍል በሞ/19 ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 በአካል በመገኘት ወይም በቢሮ ስልክ ቁጥር 0333116263፣ 0333124956 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደቡብ ወሎ ዞን የደሴ አካል ተሀድሶ ማዕከል
