የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ ሸልፍ፣ የብረት ፋይል ካቪኒት፣ ፍሪጅ፣ ቲቪ ስታንድ እና ኦቭን መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የተለያዩ ያገለገሉ ሸልፍ፣ የብረት ፋይል ካቪኒት፣ ፍሪጅ፣ ቲቪ ስታንድ እና ኦቭን መነሻ ዋጋ በማስቀመጥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በሽያጭ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተጫራቾች መስፈርት የማክበርና የመፈፀም ግዴታ አለባቸው፡፡
- ይህ ጨረታ ድርጅት ወይም ግለሰብ ሊሳተፍበት ይችላል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን እንዲሁም ቅዳሜ ግማሽ ቀን ባሉት የሥራ ቀናት ጠዋት 3፡00 እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ 7፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት ቃሊቲ ቶታል አካባቢ በሚገኘው የኢንተርፕራይዙ ቋሚ ግምጃ ቤት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ፡፡
- አንድ ተጫራች ያገለገሉ ሸልፍ ፣ የብረት ፋይል ካቪኔት ፣ ፍሪጅ ፣ ቲቪ ስታንድ እና ኦቭን አይነታቸውን መሰረት በማድረግ የሚገዛበትን የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ የሚገዛውን መጠን በማስቀመጥ መጫረት ይኖርበታል፡፡
- የዚህ ጨረታ ከተቀመጠው መነሻ ዋጋ በታች መጫረት አይቻልም፡፡ ከመነሻ ዋጋ በታች ያስገቡ ተጫራቾች በቀጥታ ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ ሲገዙ ትክክለኛ አድራሻቸውንና ሥማቸውን በመግለጽ ፈርመው መውሰድ አለባቸው።
- ጨረታው ህዳር 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው (በዕለቱ) በ 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- ኢንተርፕራዙ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዱ ጋር የመታወቂያ እና የጨረታ ሠነድ የገዙበትን ደረሰኝ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ማሳሰቢያ፡- ለሽያጭ የቀረቡት የተለያዩ ዓይነት ያገለገሉ ሸልፍ ፣ የብረት ፋይል ካቢኔት፣ ፍሪጅ ፣ቲቪ ስታንድ እና ኦቭን
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ግቢ
ስልክ ቁጥር 011-4-40-34-34
ማዞሪያ 011-4-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ info @dce-et-com
የድኅረ-ገጽ አድራሻ WWW.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ. 3414 114-40-40-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርኘራይዝ
