Tender Detail

Tender Details


በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት የሚከተሉትን ግብዓቶች 1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች 2. የጽዳት እቃ 3. የደንብ ልብስ 4. የመኪና (የተሽከርካሪ )ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል ።


የጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 9 ፋይናንስ /ቤት

የሚከተሉትን ግብዓቶች

1. አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች

2. የጽዳት እቃ

3. የደንብ ልብስ

4. የመኪና (የተሽከርካሪ )ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

2. የግብር ከፋይ መለያ ማቅረብ የሚችሉ፤

3.የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

4. የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፤

5. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ (egp/www.ppa.gov.et) ፕሪንት አድርገው መስፈርቶች በሟሟላት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

6. ጥቃቅንና አነስተኛ ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ይዘው የሚጫረቱ ተጫራቾች ከሆኑ እሴት ጨምረው ምን ዓይነት ምርት እንደሚያመርቱ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡ የሀገር ውስጥ ምርት ችርቻሮ/ ጅምላ ንግድ ከሆነ ደግሞ ከአምራች ጋር የትስስር ሰነድ እና ውል ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ካልሆነ ግን እንደ ማንኛውም ተጫራች ሰነድ ገዝተው እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ብቻ በማስያዝ መወዳደር የሚችሉ ይሆናል፡፡

7.ማንኛውም ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው እቃዎች ናሙና ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ለአላቂ ቋሚ (ለመኪና ጎማ) ለሆኑ እቃዎች በፎቶ የተደገፈ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8. በአንድ የዕቃ መግለጫ ዝርዝር ላይ ማቅረብ የሚቻለው 1(አንድ) ናሙና ብቻ ነው፡፡

 

9.ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በግልፅ በመሙላት ስርዝ ድልዝ/በፍሉድ ጠፍቶ የተፃፈ መኖር የሌለበት ሲሆን እያንዳንዱ የገዙት ሰነድ ላይ ድርጅቱን የሚገልፅ ስምና ፊርማ እና ማህተም በመምታት ኦርጅናሉንና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በሁለቱም ፖስታዎች በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በፋይናንስ ጽ/ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀበት ሳጥን ውስጥ በመቅረብ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም በ 11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው እለት ከቀኑ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡

10. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃ

1. ለሎት አንድ፡- አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች 75,700.00 ብር.(ሰባ አምስት ሺህ ሰባት መቶ ብር ብቻ)

2. ለሎት ሁለት፡- የጽዳት እቃዎች 122,770.00 ብር.(አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰባ ብር ብቻ)

3. ለሎት ሶስት፡- የደንብ ልብስ 95,500.00 ብር. (ዘጠና አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ)

4. ለሎት አራት፡- የመኪና ጎማ 8,600.00 ብር(ስምንት ሺህ ስድስት መቶ ብር ብቻ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናን አስመልከቶ ከላይ በሎት በገንዘብ መጠን በተተመነው መሰረት ከባንከ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዥያ ትእዛዝ (CPO) ብቻ አቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት በሚል አሰርተው ማቅረብ አለባቸው፡፡

11. አሸናፊ የሚሆኑት ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

12. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 ብቻ በመከፈል ዝርዝር ጉዳዮችን የያዘ የጨረታ ሰነድ በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ 4ኛ ፎቅ ላይ የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡

13. አሸናፊ የሆነው ተጫራች በራሱ ትራንስፖርትና ወጪ ያሸነፈባቸውን እቃዎችን ጥራቱ ከተረጋገጠ በኃላ ንብረት ከፍል ገቢ ያደርጋል፡፡

14. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

15. ለተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0947193350 / 0997111504 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡ አድራሻ፡- ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል በሚወስደው አስፋልት ላይ ቅሊንጦ ማረሚያ ዝቅ ብሎ ከከነማ ፋርማሲ አጠገብ ያለው ህንጻ ላይ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender