Tender Detail

Tender Details


የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዲ/ግ/ስ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018

 

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ፅ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን የተለያዩ ግዥዎችን በፑሉ ተጠቃሚ ለሆኑ መ/ቤቶች የእቃ ግዥዎችን በ6 ምድብ ከፍሎ በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡-

ሎት 1 የስፖርት ትጥቅና ግብዓት

ሎት 2 የኪቾን መገልገያ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ)

ሎት 3 የጽዳት ዕቃዎች

ሎት 4 የመዓድ ቤት ዕቃዎች

ሎት 5 የደንብ ልብስ ዕቃዎች

ሎት 6 የችግኝ ጣቢያዎች የዘር አቅርቦት ግብአቶች

ሎት 7 የግብርና የእጅ መሣሪያዎች

ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በእቃ አቅራቢ የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ከጨረታው ሰነድ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

  1. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን በማቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
  2. የጨረታ ሰነዱ በኤንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻው በፖስታ ታሽጎ የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ ማስገባት ይኖርበታል።
  3. ጨረታው እስከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ሰነዱ ተመላሽ ተደርጎ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወየም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል።
  4. ተጫራቾች በጋዜጣው ላይ በተንት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች በት ጨረታ ስሰድ ላይ ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸው።
  6.  የጨረታ ማስከበሪያ በሎት 1 ለተጠቀሰው 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እንዲሁም በሎት 2 ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ከሎት 3 እስከ ሎት 7 ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ጥቃቅን አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከሆኑ ከዳራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት ፑል የመንግሥት ግዥ ቡድን ስም ተሰርቶ መቅረብ ይኖርበታል።
  7. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ የጨረታ ዓይነቶች ውስጥ የተዘተዘሩትን የአንዱን ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ በግልጽ ከጽ/ቤት ገዝተው በወሰዱት ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ሎት 13.5 ሎት 7 በተገለፁት ጨረታ ዓይነቶች በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን እስከ 4:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ናሙና ማቅረብ ግዴታ ወደ ጽ/ቤታችን ሳንፕል ክፍል ማስገባት ይኖርባቸዋል። በሎት 4 የመዓድ ቤት ዕቃዎች በመሸጫ ቦታው ስቶክ መኖሩን እና ሳምፕል ማሳየት ይኖርባቸዋል። በሎት 2 የኪችን መገልገያ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ) ጨረታ ሰነዱ ላይ በተዘጋጀው ሰፔክ መሰረት መሙላት የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው እንደተከፈተ ስፔኩ ታይቶ ሲረጋገጥ አሸናፊው የሚለይ ይሆናል። ሌሎቹ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው ስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል።
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆኖ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ ኮ/ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የሚገኘው የክፍለ ከተማው ህንፃ 3ኛ

ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301 ስልክ ቁጥር 011 835 0897

 

የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ፅ/ቤት

Save Tender