Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsehay Industry S.C. Kaliti Metal Products Factory (ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ)
  • Address ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ከካፍደም ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 700 ሜትር ገባ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 4 34 03 87
  • Websitehttps://tsehayindustrysc.com/?page_id=8&lang=en
  • Deadline21 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security20,000.00 (ሃያ ሺ ብር)
  • opening date2025-10-21 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Industry And Factory , Used Items

ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ ከዚህ በታች የተጠቀሱት የተለያዩ 2ኛ ደረጃ ምርቶች፣ የብረት ጥሬ ዕቃ ማሸጊያዎችና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

Tsehay Industry S.C. Kaliti Metal Products Factory (ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ)


Document No.:

OF/KMPF/027 (Pr No 008)

 

ጨረታ ቁጥር 003/2018

ፀሐይ ኢንዱስትሪ አማ. ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ

የ2ኛ ደረጃ ምርቶችና ቁርጥራጭ ብረቶች ሽያጭ

የጨረታ ቁጥር 003/2018

ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ. ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ ከዚህ በታች የተጠቀሱት የተለያዩ 2ኛ ደረጃ ምርቶች፣ የብረት ጥሬ ዕቃ ማሸጊያዎችና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. 2ኛ ደረጃ
    1. የቱቦና ኤልቲዜድ ምርቶች (steel tubes and LTZ Profiles)
    2. ጥቁር ስትሪፕ እና ላሜራዎች (Strip and black flat sheet)
    3. ባለቀለም ኤጋና ሌሎች የታጠፉ ምርቶች (precoated EGA and pressed products)
  2. የብረት ማሸጊያዎች-
    1. የጥቅል ብረት ማሸጊያ ልሙጥ ዝርግ ብረቶች (Coil cover)
    2. ልዩ ልዩ ክብ የጎን የጥቅል ብረት ሽፋን
    3. ቦንዳ
  3. ቁርጥራጭ ብረቶች
    1. ከጥቅል ብረት ጠርዝ የሚወጣ ወፍራም ስትሪፕ
    2. ቁርጥራጭ ብረቶች በጥቁር፤ በጋልቫናይዝድና በባለቀለም ናቸው።

በመሆኑም ማንኛውም ተጫራች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ የሽያጭ ዋና ክፍል ዘወትር ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በስራ ስዓት በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው ጥቅምት 11 ቀን 2018 ዓ.ም. ከረፋዱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን ከረፋዱ 4፡15 ሰዓት ይከፈታል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

አድራሻ ቃሊቲ ከቶታል ማደያ ፊት ለፊት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ

ስልክ 011 4 340110/011435 16 62/435 16 92/0114 34 24 10

 

Save Tender