Tender Detail

Tender Details

  • Company Cooperative Bank of Oromia (COOP) (የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ)
  • Address Bole Sub-city, Woreda 02, Africa Avenue, Rwanda Embassy Area, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 0115 576174
  • Websitehttps://coopbankoromia.com.et/
  • Deadline03 Nov 2026, 2:00 PM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price300(ሦስት መቶ ብር)
  • Bid Securityየጠቅላላ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር 10% (አስር በመቶ)ዉን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO)
  • opening dateማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure , Disposal Sale , Used Items

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ዩፒኤሶች ፣የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፣ ጀነሬተሮች ፣ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Cooperative Bank of Oromia (COOP) (የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ አ.ማ)


የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር FA- 05/2026/27

የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ሲገለገልባቸው የነበሩ ያገለገሉ የተለያዩ አቅም ያላቸው ዩፒኤሶች ፣የተለያዩ የቢሮ ወንበሮች፣ ጠረጴዛዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ባትሪዎች፣ ያገለገሉ የመኪና ጎማዎች፣ ጀነሬተሮች ፣ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ መግዛት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች መከተል ይኖርባቸዋል: -

  1. የዕቃዎቹ ዓይነትና ዝርዝር በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ከጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ድረስ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ወይም የግብር መለያ ካርድ ያላችሁ ተጫራቾች በሌ መንገድ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ ኢጆ ቅርንጫፍ ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ ላገለገሉ ዕቃዎች ጨረታ ሰነድ መግዣ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በሂሳብ ቁጥር ETB1446500010001 በማስገባት ደረሰኙን በመያዝ የጨረታ ሰነዱን ቦሌ መንገድ ከአፍሪካ ኢንሹራንስ ፊትለፊት፣ ከባንኩ ህንጻ አጠገብ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ ከባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  2. የዕቃዎቹን ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በአካል ማየት ለሚፈልጉ ተጫራቾች የከፈሉበትን ስሊፕ እና የጨረታ ሰነዱን በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት ሱሉልታ አዲስ የተሰራዉ ክ/ከተማ ከዋና መንገድ ወደ ቀኝ 100 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ፒልከን ተብሎ በሚታወቀው የባንኩ ግምጃ ቤት ውስጥ በመገኘት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ብቻ በተቀመጠው ፕሮግራም መሠረት ፒልከን ለሚገኘው ንብረት ጥቅምት 18 ፣ 19፣ 20 እና 23 ቀን 2019 ዓ.ም ከጧቱ 3:00 ሰዓት እስከ 10:00 ሰዓት ድረስ ሲሆን በታ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  3. እንዲሁም የተቃጠለ የመኪና ዘይት ከነበርሜሉ ያለበትን ሁኔታ ለመጎብኘት ቁሩ በረት ከአልማዝዬ ሜዳ ወደ ጎፋ በሚወስደው ዋናው መንገድ 100 ሜትር እንደተጓዙ በቀኝ በኩል የባንኩ ጋራዥ ቅጥር ግቢ ውስጥ በማንኛውም የሥራ ሰዓት እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2019 ዓ.ም 10:00 ሰዓት ድረስ መጎብኘት ይችላሉ፡፡
  4. ገገርዎች የሚገዙበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ እስከ ጨረታ መዝጊያ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም 8:00 ሰዓት ድረስ ቦሌ መንገድ ራንግ ህንጻ ንብረት አስተዳደር ዋና ክፍል በአካል ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በመላክ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ በማስገባት መጫረት ይችላሉ፡፡
  5. ባንኩ የሚከተለው የማወዳደሪያ ዘዴ በሰነዱ ሰንጠረዥ ላይ ንብረቶቹ እንደተዘረዘሩት ዓይነት በተናጠል መስመር በመስመር ሲሆን ባንኩ የተሻለ ሆኖ ካገኘም በጥቅል ወይም በጅምላ ያወዳድራል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ንብረት የጠቅላላ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ጋር 10% (አስር በመቶ)ዉን በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፤ በተጨማሪም የጨረታ መነሻ ዋጋ ለሌላቸው የሚገዙበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሳይያያዝ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
  8. ተጫራች የሚገዛበት የመግዣ ዋጋ በግልጽ በዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በተቀመጠው መሠረት ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% መካተቱን ወይም አለመካተቱን ለይቶ መጻፍ ይኖርበታል፤ ነገር ግን አሻሚ ቦታ ላይ ወይም ሁለቱም ቦታ ላይ ተመሳሳይ ዋጋ ከጻፈ እና ምንም ካልተገለጸ ባንኩ የቀረበው ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተካቶ እንደቀረበ ታሳቢ ያደርጋል፡፡
  9. አሸናፊ መሆናቸው የተገለፀላቸው ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት ሙሉ ክፍያውን በአምስት ቀናት ውስጥ ከፍለው ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ካልሆነ ግን ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፖኦ ውርስ ይደረጋል፡፡
  10. ጨረታው ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም በ 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዛው ዕለት ማክሰኞ ጥቅምት 24 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ላይ ራንግ ህንጻ 7ኛ ፎቅ የስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ተጫራቾች በተገኙበት የጨረታ ሰነዱ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
  11. ባንኩ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ራንግ ህንፃ 7ኛ ፎቅ የባንኩ ንብረት አስተዳደር ዋና ቢሮ

ስልክቁጥር፡- 0115 576174 ፖ.ሳ.ቁ.16936/አዲስአበባ/

የኦሮሚያ ኅብረት ስራ ባንክ /አ.ማ/

ማህበረሰቡን ማጎልበት፣ ህይወትን መለወጥ!

✨ messages.ai_summary
Cooperative Bank of Oromia is selling used items by tender, including UPS units of various capacities, office chairs and tables, used vehicle batteries and tires, and generators, all sold as-is. Bidders must have a tax registration certificate or tax ID card.
Save Tender