የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ዕቃዎች በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞቹ ሙሉ የመድን ካሣ ከፍሎ የተረከባቸውን -
- ቀረጥ የተከፈለባቸው ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች
- ከክሬን የወረዱ የክሬን መሳሪያዎች
- ልዩ ልዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት
- የተለያዩ ብረታ ብረቶችን በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል
- ባለ ሦስት ፌዝ ትራንስፎርመር 2000 KWA ከነመለዋወጫዎቹ
ማንኛውም የስም ማዛወሪያ፣ የጉምሩክ ቀረጥ፣ ግብር፣ ተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ወጪዎች ቢኖሩ ከፍሎ በጨረታ ለመግዛት የሚፈልግ ሁሉ ቃሊቲ ክራውን ሆቴል በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል በመገኘት መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመመልከትና የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮጵያ መድን ድርጅት /Ethiopian Insurance corporation/ ስም በተሰራ ሲፒኦ በማስያዝ መጫረት ይችላል፡፡
በተጨማሪም የሰሌዳ ቁጥር EX-0109 ኤክስካቫተር ማሸነሪ በአፋር ክልል ሰምሮቢ ወረዳ ዳሊፋጊ አካባቢ ማሽኑ የወደቀበት ቦታ በወንዝ ውስጥ ሲሆን በጨረታ ስለሚሸጥ ተጫራቾች በቦታው ተገኝታችሁ መመልከት ትችላላችሁ፡፡ ተጨማሪና አዲስ መረጃ ለማግኘት ሰመራ ቅርንጫፍ ስልክ ቁጥር 0946-00-10-04 እንዲደውሉ እናሳውቃለን፡፡
ሀ/ የዕቃ ማስያዣ: የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የዕቃ ማስያዣ ብር 1000 ነው።
ለ/ የተሽከርካሪ ማስያዣ
|
የጨረታ መነሻ |
እስከ ብር 50,000.00 |
20 በመቶ |
|
ከብር 50,001.00 |
እስከ 100,000.00 |
ብር 15,000.00 |
|
ከብር 100,001.00 |
እስከ 200,000.00 |
ብር 25,000.00 |
|
ከብር 200,001.00 |
እስከ 300,000.00 |
ብር 37,000.00 |
|
ከብር 30,0001.00 |
እስከ 400,000.00 |
ብር 50,000.00 |
|
ከብር 400,001.00 |
እስከ 500,000.00 |
ብር 60,000.00 |
|
ከብር 500,001.00 |
እስከ 800,000.00 |
ብር 75,000.00 |
|
ከብር 800,001.00 |
ብር በላይ |
ብር 100,000.00 |
ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሠነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ለገሀር በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው ጥቅምት 04 ቀን 2018 ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ቃሊቲ በሚገኘው በሪከቨሪ ቴክኒክ ማዕከል ይከፈታል፡፡ በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የሥራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ተጫራቾች መክፈል ከጀመሩበት ቀን ጀምሮ በ10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ክፍያ አጠናቀው ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልከ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፣ ክፍያ ፈፅመው ንብረቶቹን በተገለፀው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 150 (አንድ መቶ ሃምሳ ብር) ይከፍላሉ፡፡
ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ተሽከርካሪም ሆን ቁሳቁስ በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011439-25-89 እና 011439-25-45 መጠየቅ ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ መድን ድርጅት
