Tender Detail

Tender Details

  • Company በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጅማ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
  • Address ጅማ ከተማ ጅማ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ፡ ኦሮሚያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 047-2-11-34-33
  • Website
  • Deadline10 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Security100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • opening date2025-10-10 00:00:00
  • Categories Machinery , Construction Machinery , Construction Vehicle

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጅማ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በሥሩ በሚገኙ ጥገና ፕሮጀክቶች ለሚሰራቸው የመንገድ ሥራዎች አገልግሎት የሚውሉ ከታች በሠንጠረዡ የተገለፁትን ማሸነሪዎችና ተሽከርካሪዎች በዋናው መ/ቤት አዲስ ተሻሽሎ በወጣው ቁርጥ ዋጋ መሠረት ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጅማ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት


 

የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ኪራይ አገልግሎት ግዥ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 04/2018 ዓ.ም

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጅማ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት በሥሩ በሚገኙ ጥገና ፕሮጀክቶች ማለትም በጊቤ - ጅማ፤ በጅማ - ቦንጋ - ሚዛን፤ በሚዛን - በቢቃ - ዲማ፤ በዋቻ - ማጂ፣ በጊንቦ - ጎጀብ -ድሪ መገንጠያ፣ በቦንጋ - ፈለገሰላም - አመያ - ጭዳ፣ በዲዴሳ ወንዝ 1 - የምበሮ - በደሌ፣ በዲዴሳ ወንዝ 2 - በደሌ፤ በሎኮ ድልድይ ግንባታ፣ በመቱ - አልጌ፣ በሙቱ - ሶር፣ በመቱ - ጋምቤላ - ኢታንግ፤ በሲግሞ ከተማ ፕሮጀክቶች ለሚሰራቸው የመንገድ ሥራዎች አገልግሎት የሚውሉ ከታች በሠንጠረዡ የተገለፁትን ማሸነሪዎችና ተሽከርካሪዎች በዋናው መ/ቤት አዲስ ተሻሽሎ በወጣው ቁርጥ ዋጋ መሠረት ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

 

ተ/ቁ

የማሽነሪው/ የተሽከርካሪው ዓይነት

የስሪት ዘመን

ብዛት

1

ገልባጭ መኪና

2012 ጀምሮ

40

2

ኤክስካቫተር ባለ ጃክ ሃመር

2012 ጀምሮ

6

3

ኤክስካቫተር ባለ አካፋ

2012 ጀምሮ

6

4

ዊል ኤክስካቫተር

2012 ጀምሮ

4

5

ዶዘር

2012 ጀምሮ

1

6

ግሬደር

2012 ጀምሮ

6

7

ዊል ሎደር

2012 ጀምሮ

10

8

ሮለር ሲንግል ድራም

2012 ጀምሮ

6

9

ሮለር ደብል ድራም

2012 ጀምሮ

4

10

የውሃ ቦቴ

2010 ጀምሮ

6

 

በዚሁ መሠረት ማሽነሪዎችንና ተሽከርካሪዎችን ለማከራየት የምትፈልጉ አከራዮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በማንኛውም የሥራ ሰዓት (ቅዳሜ ሙሉ ቀን ጨምሮ) ጅማ ዩኒቨርስቲ አጠገብ በስተግራ በሚገኘው ዲስትሪክታችን ግዥ፣ አቅርቦትና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 (አራት) በአካል ቀርባችሁ የመጫረቻ ሠነድ ገዝታችሁ መሣተፍ የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን አከራዮች በጨረታው ለመሳተፍ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል፡፡

  1. በምዝገባው መሣተፍ የሚችሉ አከራዮች ማሽነሪዎቻቸውንና ተሽከርካሪዎቻቸውን እንዲያሰማሩ ትዕዛዝ በደረሳቸው በአንድ (1) ሣምንት ጊዜ ውስጥ በሥራ ቦታው መድረስ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  2. ለመጫረት የሚፈልጉ አከራዮች የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ እና 2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin No) ያለው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ አራት መቶ (400.00) ብር በሂሣብ ቁጥር ERA Jimma Road Maintenance District "B" 1000322277958 በመክፈል ሠነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ሠነድ ውስጥ በተያያዘው የዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ በመሙላት የድርጅታቸውን ማህተምና የተወካይ ፊርማ በማድረግ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል በኮፒ እና በኦሪጅናል ዶክመንት ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተጠቀሰው አድራሻ እና ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች/ ማስረጃዎች አሟልተው የቀረቡ አከራዮች ለምዝገባው የሚቀርቡት ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች የስሪት ዘመን ከላይ በሠንጠረዡ በተጠቀሰው መሠረት መሆን አለበት፡፡
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ጅማ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ በሚገኘው የሠራተኞች መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  9. ዲስትሪክቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ተመዝጋቢዎች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡

ጅማ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ስልክ ቁጥር 047-2-11-34-33

 

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጅማ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት

 

Save Tender