በጅማ ዞን መንቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የግል ድርጅቶች እና ጥቃቅንና አነስተኞችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የመንገድ ግንባታ ሥራ ማሽኖችን፣ ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሮለር፣ ሎደር፣ ሎቤድ፣ ሻወርትራክ፣ ባክ-ሎደር እና ሲኖትራክ ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በጅማ ዞን የመንቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በጅማ ዞን መንቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት የግል ድርጅቶች እና ጥቃቅንና አነስተኞችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ የመንገድ ግንባታ ሥራ ማሽኖችን፣ ዶዘር፣ ኤክስካቫተር፣ ግሬደር፣ ሮለር፣ ሎደር፣ ሎቤድ፣ ሻወርትራክ፣ ባክ-ሎደር እና ሲኖትራክ ተከራይቶ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት የመወዳደሪያ መሥፈርቶች፡-
- በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- በንግድና ከተማ ልማት ጽ/ቤት በስነ-ስርዓት ጉድለት ያልተከሠሡ፤
- የግብር መለያ ቁጥር (TIN No) ማቅረብ የሚችሉ፤
- የፌዴራል እና ክልል የፋይናንስ ግዢ ስርዓት አስተዳዳር የሚያከብሩ፤
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- ተወዳዳሪዎች የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተወዳዳሪው በሰነዱ ላይ ትክክለኛ አድራሻ፣ ስም እና ፊርማ ማሳረፍ አለባቸው፡፡
- የጨረታው ማስከበሪያ ማረጋገጫ የሚሆን 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችሉ፤
- ጨረታውን ያሸነፈው አካል ህጉ በሚፈቅደው መሠረት 2% (ሁለት ፐርሰንት) የመክፈል ግዴታ አለበት።
- ጨረታው የሚከናወነው ሰነዱ በወጣበት ቋንቋ መሠረት ይሆናል፡፡
- ሁሉም ተወዳዳሪዎች ከጨረታው ሰነድ አንድም ገጽ ሳያጎሉ ሞልተው መመለስ አለባቸው።
- ተወዳዳሪው በተወሰነለት ጊዜ ውስጥ የተፈለገውን ማሽኖችን ብዛት እና ጥራት ደረጃውን በጠበቀ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተወዳዳሪዎች ለማሽኑ የሚያስፈልገውን ነዳጅ ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ስራው እንዳይቆም ሲባል ተወዳዳሪው እውቅና ካለውና ጨረታው የሚከናወንበት አካባቢ ወይም ለወረዳ ቅርብ ከሆነው ሼል (ማደያ) ዋስትና ማቅረብ አለበት፡፡
- ተወዳዳሪው የማሽኖች የባለቤትነት (ሊብሬ) ማቅረብ ወይም ከሌላ አካል ተከራይቶ ከሆነ መከራየቱን የሚያሳይ የአከራይና ተከራይ ውል በህገ አቃቤ ማህተም የተረጋገጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የማሽኑ አገልግሎት ዘመን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2016-2018 እና ከዚያ በላይ መሆን አለበት፡፡
- ሰነዱ የቴክኒክ እና ፋይናንሻል ኦሪጅናልና ኮፒ ለየብቻ (4 ፖስታ) በአንድ ፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለባቸው።
- ሌላ ቦታ የሰራበትን የሥራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተወዳዳሪው የታደሰ የማሽን አከራይነት ማስረጃ ከክልል ኮንስትራከሽን ወይም ፋይናንስ ቢሮ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ከላይ የተዘረዘሩት ነጥቦች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች ከቀን 08/01/2018 እስከ 28/01/2018 ዓ.ም ከመንቾ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቀርባችሁ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር) ከፍላችሁ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ትችላላችሁ፡፡
- የጨረታው ሰነድ ሳጥን በቀን 28/01/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት የሚዘጋ ሆኖ የሚከፈተው በዛው ቀን ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ተወካዮች በተገኙበት በ4፡30 ሰዓት ይሆናል፡፡
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09-35-08-19-63/ 09-02-16-25-76
በጅማ ዞን የመንቾ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
