Tender Detail

Tender Details

  • Company የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ቴፒ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0924286400
  • Website
  • Deadline17 Nov 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Priceለእያንዳንዱ ሎት ብር 500
  • Bid Securityሎት 1 ብር 20,000፤ ሎት 2 ብር 10,000፤ ሎት 3 ብር 15,000 (CPO ወይም ጥሬ ገንዘብ)
  • opening dateበዕለቱ 4:30
  • Categories Road And Bridge Construction , Building Construction

የቴ/ከ/አ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ር የስራ ሂደት የቴፒ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በመሰረተ ልማት ማስፋፊያ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በግልፅ ጨረታ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የቴፒ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት


ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የቴ/ከ/አ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ር የስራ ሂደት የቴፒ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በመሰረተ ልማት ማስፋፊያ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በግልፅ ጨረታ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ [የመግቢያው ክፍል ከፎቶው በከፊል የማይነበብ]

ሎት 1 የፍሳሽ ማስወገጃ ዲች ግንባታ (Massonary Drainge)፡-

  • 1.1/ አንድነት ቀበሌ ከአቶ ዜማ ቤት መምሪያ ቤት እስከ 3ቢ መንገድ ፊት ለፊት ድረስ 200ሜ
  • 1.2/ የፍሳሽ ማስወገጃ ዲች በይ (Massonary Drainge) ህብረት ቀበሌ ከአህመድ ሶቢራ እስከ መቋቋት የአህል መጋዘን ድረስ 160ሜ
  • 1.3 የፍሳሽ ማስወገጃ ዲች በይ (Massonary Drainge) ህብረት ቀበሌ ከአወል ጀሮ የአህል መጋዘን ፊት ለፊት እስከ ትንሽዋ ድልድይ ድረስ 250ሜ
  • 1.4 የፍሳሽ ማስወገጃ ዲች በይ (Massonary Drainge) ሠላም ቀበሌ ከሴቶች ወፍጮ ቤት እስከ ሙንጫ ወንዝ መንገድ 8 ድረስ 300ሜ
  • 1.5 የፍሳሽ ማስወገጃ ዲች በይ (Massonary Drainge) አንድነት ቀበሌ ከውሃ ልማት እስከ ያረጋል ሱቅ ፊት ለፊት ድረስ 275ሜ
  • 1.6 የፍሳሽ ማስወገጃ ዲች በይ (Massonary Drainge) ህብረት ቀበሌ ከአቶ ፈለቀ ህንጻ እስከ በደሩ ኪራጋ ፊት ለፊት ድረስ 120ሜ

ሎት 2 ካልቨርት ግንባታ፡-

  • 2.1/ ሠላም ቀበሌ ቁጥር 2 ት/ቤት ፊት ለፊት 10ሜ
  • 2.2/ አንድነት ቀበሌ ሚሊኒየም ጉዳና እና ሚካኤል ቤ/ን ፊት ለፊት 12 ሜ
  • 2.3/ ሠላም ቀበሌ 30 ሠፈር 10ሜ

ሎት 3 የህዝብ መፀዳጃ ሽንት ቤት፡-

  • 3.1 የገበያ ሜዳ መሃል ባለ 6 ክፍል ሻወር እና ሽንት ቤት 2 ብሎክ ስሆን

በዚሁ መሰረት በጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በተሰማሩበት የግንባታ ስራ ዘርፍ ለ2019 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ አለባቸው።
  2. የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የቫት (ተጨማሪ እሴት ታክስ) ምዝገባ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች በተቋራጭነት አስፈላጊ የተደራጁበትን የሙያ ማህበር ህጋዊ ሰውነት ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የ2019 የታደሰ ደረጃ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  6. ተጫራቾች የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው፡፡
  7. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም ግብር ስለመክፈላቸው ከገቢዎች የክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው።
  8. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሲፒኦ (CPO) ሎት አንድ (1) ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) ሎት 2 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) ሎት 3 15,000 (አስራ አምስት ሺ) ብር በባንክ የተረጋገጠ ወይም በጥሬ ገንዘብ ቴፒ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
  9. ተጫራቾች ማህበር ከሆኑ አባል የሆኑትን የሁሉም የTVT Collage ወይም ዲግሪ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች ጨረታውን ሲያሸንፉ ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ውል ማስከበሪያ 10% ሲፒኦ (CPO) ከታወቀ ባንክ ለማቅረብ ፍቃደኛ የሆነ።
  11. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን 1(አንድ) ኦርጅናል እና 2(ሁለት ኮፒ) በተለያየ ፖስታ በማሸግ በዕቅቱ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ማስገባት ይችላሉ።
  12. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 21/ ሃያ አንድ /ተከታታይ ቀናት ጨረታው በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ22ኛ ሁለተኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ላይ ከተማ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቴፒ ከተማ ፋ/ጽ/ቤት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሃያ ሁለተኛው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
  13. የድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ በፖስታ ላይ እና በእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ ላይ እንዲያርፍ ይደረጋል።
  14. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከቴ/ከ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ/ን/አስ/ር የስራ ሂደት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 45 በመቅረብ ለዲች የድ ግንባታ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) ለካልቨርት ግንባታ 500 (አምስት መቶ ብር) ለህዝብ ሽንት ቤት አምስት 500 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
  15. አንድ ማህበር ከአንድ የጨረታ ሰነድ በላይ መግዛት አይችልም።
  16. ተጫራቾች ማህበር ከሆኑ ከአደራጅ መ/ቤት ስራ እንደሌላቸውና የአምስት አባላት ስም ዝርዝር የሚገልፅ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ከአደራጅ መ/ቤት የሚመጣው የድጋፍ ደብዳቤ የማህበር አባላት ስም ዝርዝር ካልተገለፀ ተቀባይነት አይኖረውም።
  17. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሰዓቱ ካልተገኙ የመ/ቤቱ ጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  18. ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  19. ማንኛውም ማህበር በግለሰብ ስም የሚሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) ተቀባይነት የለውም።

በደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ሸካ ዞን የቴፒ ከተማ ፋይናንስ ጽ/ቤት

✨ messages.ai_summary
Tepi City Finance Office seeks contractors for infrastructure projects via open tender: Lot 1 masonry drainage ditches, Lot 2 culvert construction, Lot 3 public shower/toilet blocks. Bidders must submit renewed business license, tax and VAT registration, professional association certificate, supplier certificate, and tax clearance.
Save Tender