Tender Detail

Tender Details

  • Company የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0462128588
  • Website
  • Deadline18 Sep 2025, 12:00 AM
  • magazine አዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid Securityለእያንዳንዱ ማሽነሪ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)
  • opening date2025-09-18 00:00:00
  • Categories Construction Machinery , Construction Vehicle

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2018 በጀት አመት ለመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውሉ ከታች የተገለፁትን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ትራኮች በሰዓት የኪራይ አገልግሎት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

የሲዳማ መንገዶች ባለስልጣን (Sidama Roads Authority)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥው መለያ ቁጥር አአከመባ/ግብዓት/ቡ-2/002-1/2018

 

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በ2018 በጀት አመት ለመንገድ ግንባታ እና ጥገና አገልግሎት የሚውሉ ከታች የተገለፁትን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች እና ትራኮች በሰዓት የኪራይ አገልግሎት በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል፡፡

 

ተ.ቁ

በሰዓት ለኪራይ የተፈለገ የማሽነሪ ዓይነት

የስሪት ዘመን እ.ኤ.አ (G.C)

ብዛት

አጠቃላይ ለኪራይ የሚፈለገው ሰዓት

የጨረታ መለያ ቁጥር

ጨረታ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ በብር

1

Dozer (≥300 Hp)

≥2012 GC

9

 

 

እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም

 

አአከመባ/ግብዓት/ቡ-2/002-1/2018

 

 

 

60 ቀን

 

 

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00

 

 

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30

 

 

ለአንድ ማሽነሪ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

2

Motor Grader (≥140 Hp)

≥2012 GC

12

3

Chain Excavator (Bucket) ≥1.6m³ heaped and ≥200Hp)

≥2012 GC

31

4

Chain Excavator (Jack Hammer) ≥200 Hp, for jack hammer min. operating weight shall be ≥2500 kg and min. impact rate shall be ≥ 350 bpm)

≥2012 GC

16

5

Wheel Excavator ≥ 1M³ Bucket capacity and 135 HP

≥2003 GC

9

6

Single Drum Roller (≥16 ton)

≥2008 GC

9

7

Double Drum Roller 4 Ton

≥2008 GC

6

8

Pneumatic Roller (≥12 ton (Unbal-lasted)

≥2003 GC

3

9

Backhoe Loader (≥1M³ front Bucket capacity, ≥ 0.5 M³ Backhoe bucket capacity, ≥90 Hp)

≥2005 GC

14

10

Asphalt Paver (paving width 22.5m without screed, Engine capacity ≥150 hp, wheeled/chain drive)

≥2005 GC

2

11

Water trucks ≥13,000Lit.

≥2010 GC

13

 

 

እስከ መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም

 

አአከመባ/ግብዓት/ቡ-2/002-1/2018

 

 

 

60 ቀን

 

 

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00

 

 

መስከረም 8 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡30

 

 

ለአንድ ማሽነሪ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር)

12

low-bed ≥50 Ton

≥2010 GC

2

13

Curve stone Machine minimum working hours 30-90 m/hr

≥2012 GC

1

14

Mixer truck minimum=7 M³ net

≥2012 GC

7

15

Compressor rated operating pressure min. 0.69 Mpa free air delivery min 7.5 M³/min

≥2012 GC

2

 

ስለዚህ፤

  1. ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፤ አግባብነት ያለው የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ከአዲስ አበባ ከተማ ኮንስትራክሽን ቢሮ፤ የግብር ከፋይ ሰርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ታክስ ክሊራንስ ሰርተፍኬት እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገፅ (WWW.PPA.gov.et) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ ተጫራቾች በሰዓት በኪራይ አገልግሎት የሚወዳደሩባቸው የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫ ምዝገባ ኤጀንሲ /ውክልና ማስረጃ/ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ የሚችሉ ስለመሆኑ በጨረታ ሰነዱ ክፍል 6 /ስድስት/ አባሪ ሁለት በቀረበው ቅፅ መሰረት በማረጋገጥ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከባለሥልጣን መ/ቤቱ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋስትናው ከታወቀ ባንክ ጋራንቲ ወይም በCertified Payment Order (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ተጫራቾች ባቀረቡት የማሽነሪ ብዛት መጠን የሚወሰን ሲሆን፤ ባለስልጣን መ/ቤቱ የተፈለገውን የማሽነሪ ብዛት በሙሉ የሚያቀርቡት የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀ መሰረት ለእያንዳንዱ ማሽነሪ 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ይሆናል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ120 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
  4. ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 104 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዥ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።

 

መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

(ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አጠገብ)

ስልክ ቁጥር፡- 011-3-72-28-25

 

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን

 

Save Tender