Tender Detail

Tender Details


የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅንና በስሩ ለሚገኙ ቅ/ፍ/ጽ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውል ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ አገልግሎቶች እና እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር:- PSSSA/AAR/01/2018

 

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅንና በስሩ ለሚገኙ ቅ/ፍ/ጽ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውል፡

ሎት 1 የደንብ ልብስና ልብስ ስፌት

ለት 2 የእስቴሽነሪ /ጽህፈት ዕቃዎች

ሎት 3 የጽዳት እቃዎች

ሎት 4 የመኪና ጎማና ቅባት እቃዎች

ሎት 5 ቋሚ እቃዎች

ሎት 6 ህትመት

መ/ቤታችን ከላይ ከሎት 1 እስከ ሎት 5 ያሉትን እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባችኋል፡፡

  1. ተጫራቾች ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ የንግድ ምዝገባ ፣ የግብር ከፋይነት ሰርትፍኬት/Tin Number/ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት ክሊራንስ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ በሚገኘው ዋስትና ንግድ ማዕከል ህንጻ ግራውንድ ላይ በመምጣት በእንድ ሎት የማይመለስ 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  3. በመ/ቤታችን ስም ማለትም public servant social security administration AA region/ የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ ብር በአንድ ሎት 3000.00 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
  4. ጨረታው ፀንቶ መቆያ ጊዜ 60 ቀን በመሆኑ አሸናፊ ድርጅቶች የአሸናፊነት ደብዳቤ በደረሳችሁ በ 15 ቀን ውስጥ ያሸነፉብትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ በማስያዝ ውል መያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  5. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ከላይ በተራ ቁጥር 2 በተገለጸው አድራሻ ከጥዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው ሳጥን ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ የተወዳደሩበትን የጨረታ አይነት፣ የድርጅቱን ስም እና አድራሻ በመፃፍ ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡
  6. ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡15 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባልተገኙበት ይከፈታል፡፡ በ16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
  7. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ፒያሳ ከጣይቱ ሆቴል ጀርባ ዋስትና የንግድ ማእከል ግራውንድ ላይ እንገኛለን፡፡

 

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-1-11-23-13

 

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር

 

Save Tender