Tender Detail

Tender Details


በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ ወረዳ መስተዳደር የዶዶላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በምዕራብ አርሲ ዞን በዶዶላ ወረዳ መስተዳደር የዶዶላ ወረዳ ገንዘብ /ቤት 2018 . የበጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለፁትን ዕቃዎችና አገልግሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች፣ ዳት ዕቃዎች፣ አላቂ ዕቃና የትምህርት ዕቃዎች
  2. የተለያዩ ኤሌክትሮንክስ ዕቃዎችና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች
  3. የሠራተኛ ደንብ ልብስ
  4. የተለያዩ የመኪና ጎማ
  5. የስፌት አገልግሎት

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናቸው፡፡

  1. ተጫራቾች ከሚጫረቱበት ዕቃ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያለውና ዕቃዎቹን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ህጋዊ ንግድ ፍቃድ፡ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡ VAT እና TIN NO. እንዲሁም የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ብቻ
  2. ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የምትፈልጉት በምን ዓይነት ዕቃ እንደሆነ በሰነዶቻቸው ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የዕቃ ስም/ Brand Name/ የተመረተበትን ሀገር መግለጽ ይኖርባቸዋል
  4. ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደርበትን የዕቃ ዓይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅርብ ይኖርበታል፡፡ በነጠላ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር የነጠላ ዋጋ ይወሰዳል፡፡
  5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀናት ውስጥ ቅዳሜ እሁድና የበዓል ቀን ሳይጨምር በተ. 1,2,3,45 የማይመለስ 800.00 ብር በዶዶላ ወረዳ አገር ውስጥ ገቢዎች ባለስልጣን በመፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸው ላይ /ቤታችን በሰጣቸው የጨረታ ሰነድ ላይ ያአንዱ ዋጋ የሚለው ቦታ ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማህተም በየገፁ፤ ፊርማና ሙሉ አድራሻውን በመግለፅ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በሥራ ሰዓት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ለጨረታ ከቀረቡ ዕቃዎች ዝርዝር ውስጥ /ቤቱ እስከ 20% ለመጨመር ወይም ለመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን በተ. 1,2,3 4 ብር 20,000.00 እንዲሁም በተ. 5 5000.00 ብር በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ወይም ጥሬ ብር በዶዶላ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ማስያዝ አለበት፡፡
  9. የሚያቀርቡት ዕቃዎች ጥራት ያላቸውና በተሰጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት ተሟልተው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ውል በሚፈርሙበት ጊዜ አጠቃላይ ከሸነፉት ዕቃ ላይ የውል ማስከበሪያ ተመላሽ የሚሆን 10% በጽ/ቤቱ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  10. አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ዶዶላ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  11. በተ. 1, 2 3 ውስጥ በመ/ቤታችን የተገለፁት ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የሚመለስ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
  12. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 የስራ ቀናት ቅዳሜ እሁድና የበዓለት ቀን ሳይጨምር አየር ላይ ከዋላ ቡሃላ 16ኛው ቀን ከጧቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጧቱ 4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመ/ቤችን ቢሮ ቁጥር 5 ውስጥ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግድም፡፡ ዕለቱ በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
  13. /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  14. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0913529429/0910408490/0911867793 ደውለው መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

በምዕራብ አርሲ ዞን የዶዶ ወረዳ ገንዘብ /ቤት

 

Save Tender