የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 ዓ/ም የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን አላቂ፤ ቋሚ እቃዎች፤ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለዞኑ ሴክተር መ/ቤት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በ 2018 ዓ/ም የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን አላቂ፤ ቋሚ እቃዎች፤ የመኪና ጎማዎች እና የሰራተኞች ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለዞኑ ሴክተር መ/ቤት ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ እና በተወዳዳሪዎች መመሪያ መሠረት ተጫራቾች ቀርበው እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል፡፡
-
ጥራት ያላቸውን ዕቃዎች ማቅረብ የሚችሉና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤
-
በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል የምዝገባ የምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ህጋዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ፤ K
-
የ2017 ዓ /ም ግብር አጠናቅቀው የከፈሉበትን ማስረጃ የሚያቀርቡና ለታክስ ከፋይነት (TIN) የተመዘገቡና ተጨማሪ ታክስ (VAT) ከፋይ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ የሚያቀርቡ ፤
-
ለጨረታ ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት ዋጋ 2% በተረጋገጠ (CPO) ከማስረጃቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፤
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር (200) በመከፈል የግዥ ክፍል ከመ/ቤቱ (G+1) ምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ፅ/ቤት መግዛት ይችላሉ፤
-
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዱን ምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብና ፅ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤
-
ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዕቃ ዓይነት የቢሮ ዕቃ መሆኑን እንደዚሁም የድርጅቱን ስም በሚያቀርቡት የተለያየ ፖስታ ላይ በኦሪጅናሉና በኮፒው ላይ በግልጽ በመጻፍ በድርጅቱ ማህተም እና ፊርማ አስደግፈው ማቅረብ አለባቸው፤
-
ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
-
ተወዳዳሪዎች ናሙና እንዲቀርብባቸው የተጠየቁትን ዕቃሙሉ በሙሉ ማቅረብና ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ቆጥሮ ማስረከብ አለባቸው፡፡
-
ጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ ስድስተኛው የስራ ቀን፣ ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ 8፡30 (በስምንት ሰዓት ተኩል) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤
-
ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሲሆኑ ዕቃዎቹን በራሳቸው ማጓጓዣ እስከ ገዥው ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፤
-
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0577712547 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፤
-
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የምዕራብ ወለጋ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ግምቢ
